መንግስትን በሃይል ለማውረድ የሚንቀሳቀሱ 3 ድርጅቶች ወደ ውህደት የሚያደርሳቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

ነሃሴ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ የግንቦት 7፣የፍትህ፣የነፃነትናየዲሞክራሲ ንቅናቄ እንዲሁም የአማራ

ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ በጋራ ባወጡት መግለጫ ”  ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ካሉበት አዘቅት በማውጣት ሕዝቡ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን

ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋዕትነት የግድ የሚለን ደረጃ ላይ ደርሰናል ብለዋል።

ድርጅቶቹ አያይዘውም ” አገራችንና ሕዝባችንን ከአዘቅት ለማውጣት በመጣመር ብቻ ሳይሆን በውህደት አንድ ሆነን አገራችንንና ሕዝባችንን አንድ በማድረጉ ረገድአስፈላጊውመስዋዕትነትበመክፈልየትግልእድሜእናሳጥርበሚልለውህደትየሚያደርሰንንውይይት ለመጀመር የሚያስችል ሂደቶችን

አጠናቀን ወሳኝ ወደሆነው ሂደት ውስጥ መግባታችንን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ወዳጆች ማብሰር እንፈልጋለን።” ብለዋል።

ከዚህ በሁዋላ በሚኖረውየሽግግርሂደትወቅትምበሁሉምየትግልዘርፍበጋራመሥራት መጀመራቸውን ድርጀቶቹ ገልጸዋል።

የውህደቱን ስምምነት በተመለከተ ጥያቄ ያደረግልናቸው የሶስቱ ድርጀቶች ተወካዮች፣ ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልካም ዜና መሆኑን ተናግረዋል።

የውህደት ስምምነቱ የኢትዮጵያን ህዝብ የሚወክል ነው ያሉት የአርበኞች ግንባር የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አርበኛ መንግስቱ፣ ወ/ስላሴ፣ ትግላችን መስዋትነትን

በሚጠይቅ ትግል ላይ የተመሰረተ መሆኑ ውህደቱን ኢትዮጵያዊ ያደርገዋል ብለዋል

የግንቦት7 ህዝባዊ እምቢተኝነት ዘረፍ ሊ/መንበርና የስራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት አቶ አበበ ቦጋለ በበኩላቸው የሶስቱ ድርጅቶች ውህደት እንደተጠናቀቀ

ከሌሎች ድርጅቶች በተለይም ከትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት ( ትህዴን ) ጋር በጥምረት የሚሰራበት ስራ ይጀመራል ሲሉ ገልጸዋል።

ውህደቱ ሲጠናቀቅ በአንድ አመራር ስር እንደሚሆን ሌላው የውህዱ ድርጅት አባል የሆነው የአማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ተወካይ ታጋይ ተፈሪ ካሳሁን ገልጿል።

ሶስቱም ድርጅቶች የኢትዮጵያ ህዝብ ትግሉን እንዲደግፍ በተለይም የመከላከያ ሰራዊት አባላት አዲሱን ውህድ ሃይል ተቀላቅለው ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነትና

ለነጻነት የሚደረገውን ትግል እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል። ከሶስቱም መሪዎች ጋር የተደረገው ቃለምልልስ ሰሞኑን ይቀርባል።