መቶሺዎች የተሰውበትን የሶሪያን ጦርነት ለማስቆም ድርድር ተጀመረ

ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሶሪያ መንግስት እና የተቃዋሚዎች ተደራዳሪዎች በስዊዘርላንድ የተሰበሰቡ ሲሆን ፣ሁለቱም ተደራዳሪዎች ከማለዳው ሃይለ ቃሎችን ተለዋውጠዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሁለቱም ተደራዳሪዎች ወደ ገንቢ ውይይት እንዲመጡ ቢጠይቁም እስካሁን ተስፋ የሚሰጥ ነገር አልተገኘም።

አንዱ እና ዋናው አጀንዳ ፕሬዚዳንት በሽር አላሳድ ስልጣን ላይ ስለመቆየታው ሲሆን፣ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጆን ኬሪ ፕሬዚዳንት ባሽር ስልጣን ላይ የሚቆዩበት ምንም አይነት መንገድ መኖር የለበትም ብለዋል። የሶሪያ ጦርነት የመቶ ሺዎችን ህይወት አስገብሯል  ለሚሊዮኖች መፈናቀልም ምክንያት ሆኗል። ግጭቱ