መምህር ስዩም ተሾመና አቶ ታዬ ደንደዓ ከእስር ተለቀቁ

መምህር ስዩም ተሾመና አቶ ታዬ ደንደዓ ከእስር ተለቀቁ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 08 ቀን 2010 ዓ/ም) በማህበራዊ ሚዲያ ሃሳቡን በድፍረት በመግለጽ የሚታወቀው መምህር ስዩም ተሾመ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፎ አገዛዙን ተቃውሟል በሚል ለወር ያክል ጊዜ ከታሰረ በሁዋላ ዛሬ ከእስር ቤት ተለቋል። በተመሳሳይ መንገድ የታሰረው የኦሮምያ ፍትህ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ታዬ ደንደዓም እንዲሁ ከእስር ተለቋል።
ሁለቱ ታዋቂ ሰዎች ከእስር እንዲፈቱ በማህበራዊ ሚዲያ ተደጋጋሚ ቅስቀሳ ሲካሄድ ቆይቷል። አቶ ታዬ በሞያሌ በወታደሮች የተገደሉ 13 ሰዎች ሆን ተብሎ እንደተገደሉ እንደሚሰማቸው ለተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ገልጸው ነበር።
ምንም እንኳ ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴውን ተከትሎ ኢህአዴግ ታዋቂ የሆኑ የህሊና እስረኞችን ቢፈታም፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ አሁንም በርካታ የህሊና እሰረኞች በእስር ላይ ይገኛሉ።