ህዳር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ለኢትዮጲያ መንግስት የሚያገለግሉ የፌደራል ፓሊስ አባላት እየከዱ መሆናቸውን እንዲሁም በሁመራና በመተማ ወታደራዊ ግጭቶች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን አንድ የፌደራል ፓሊስ ሃላኢ ገለፁ። ይህም በምስልና በድምፅ ይፋ ሆኗል። በሌላምበኩል በሰሜን ኢትዮጲያ ጠረፋማ አከባቢዎች ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች አንዱ የሆነው ትሕዴን ሰራዊቱን በክፍለ ጦር ደረጃ ማዋቀሩን ለቀመንበሩ ለኢሳት ገልፀዋል።
በምስራቅ ኢትዮጲያ በኦጋዴን አከባቢ የፌደራል ፖሊስ አባላትን ሰብስበው ገለፃ ያደረጉት የፌደራል ፖሊስ ሃላፊ ፖሊሶች እየከዱ ማስቸገራቸውን ገልፀዋል። ለሰባት ዓመታት ለማገልገል የገቡትን ሥምምነት ጥሰው በመኮብለላቸው እየያዝን ጅጅጋ እስር ቤት እንከታቸዋለን ሲሉ አሳስበዋል። በምስራቅ ካለው ይልቅ የሰሜኑ ችግር የሰፋ መሆኑን በሁመራና በመተማ ዘወትር ግጭት በመታየት ላይ መሆኑን አብራርተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም በሰሜን ኢትዮጲያ ነፍጥ ካነሡት ሃይሎች አንዱ የሆነው ትሕዴን ተከታታይ ወታደራዊ ጥቃት ሲያደርስ መቆየቱን ሊቀመንበሩ አስታውቀዋል። የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትሕዴን) ሊቀመንበር ታጋይ ሞላ አስገዶም ለኢሳት በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት ትሕዴን ወታደራዊ ተጠናክሯል ከሌሎች የኢትዮጲያ ሃይሎች ጋር ግንባር በመፍጠርም በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት በሃይል ለመጣል እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አመልክተዋል ።