ኀዳር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህገመንግስቱ የጸደቀበት በተለምዶ የብሄር ብሄረሰቦች በአል ህዳር 29 ቀን በጋምቤላ ክልል የሚከበር ሲሆን ፣ ለበአሉ ድምቀት በጋምቤላ ስታዲየም ተገንብቷል። ከ5 ሺ በላይ እንግዶችን ለማስተናገድ የማሰልጠኛ ተቁዋማት የመማሪያ ክፍሎችን ጭምር ወደ ምኝታ ክፍሎች ለመቀየር ታስቦአል።
በፈዴሬሽን ም/ቤት በኩል በየአመቱ ከ200 ሚሊየን ብር በላይ የሚወጣበት ይህ በአል ፣ዘንድሮ ከ15 ሚሊየን በላይ ወገኖች በድርቅ ችግር ውስጥ በሚማቅቁበት ወቅት ይከበራል።