ለምግብ እጥረት ተጠቂ ለሆኑ የኢትዮጵያ አዛውንቶች ቅድሚያ እንዲሰጥ ሲል ተመድ አሳሰበ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 11 ቀን 2010 ዓ/ም) የኢትዮጵያ መንግስትና ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ለጋሾች በአገሪቱ ላሉ የተመጣጠነ የምግብ እጥረት ተጠቂ ለሆኑ አዛውንቶች ቅድሚያ በመስጠት ሕይወታቸውን ሊታደጓቸው ይገባል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ቀውስ ቡድን ማሳሰቢያ ሰጠ።
በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የሚገኙ አገራት የስጊ የድርቅ አደጋ አንዣቧል። ከፍተኛውን የርሃብ አደጋ ካንዣበባቸው አገራት ውስጥ ኢትዮጵያ ከፍተኛውን ቁጥር ያላቸው ተጠቂዎች ያሉባት አገር መሆኗን ሪፖርቱ ጠቁሞ እድሜያቸው ለገፉ ዜጎች የሚሰጠው ትኩረት አናሳ ነው ብሏል።
በእድሜ የገፉ አዛውንቶች የተለየ ክትትልና የተመጣጠነ ምግብ ያስፈልጋቸውና ለመብላትና ለማላመጥ የሚችሉት የተለየየምግብ ዓይነት ሊቀርቡላቸው ይገባል። የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚሰጡ የረድኤት ቡድኖች ይህን በመረዳት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ሪሊፍ ዌብ ዘግቧል።