ለመጀመሪያ ጊዜ ለውጭ የደህንነት ሰራተኞች ደሞዝ በብር ተከፈለ

ታኅሣሥ ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት የውጭ ደህንነት ሰራተኞች ከዚህ ቀደም ተደርጎ በማያውቅ ሁኔታ ደሞዛቸው በብር እንዲከፈላቸው ተደርጓል።

እስካሁን ድረስ ደሞዝ ይከፈለው የነበረው በአሜሪካን ዶላር ቢሆንም፣ በዚህ ወር ግን ዶላር የለም በሚል ምክንያት በብር እንዲከፈለን ተደርጓል ሲሉ ለኢሳት ተናግረዋል። በጎረቤት አገራት በደህንነት መረጃ ማሰባሰብ ስራ ላይ ከተሰማሩት የደህንነት ሰራተኞች መካከል ብዙዎቹ ከብሄራቸው ጋር በተያያዘ ከሚፈጸምባቸው አድልዎ በተጨማሪ፣ በቂ ክፍያ ባለማግኘታቸው ስራቸውን እየለቀቁ ስደትን እንዳማራጭ እየወሰዱት ነው።

በኢትዮጵያ ከተነሳው ህዝባዊ አመጽ ጋር በተያያዘ የዶላር ዋጋ ያሻቀበ ሲሆን፣ በባንክ የአንድ ዶላር ዋጋ በ22 ብር ሲመዘር በጥቁር ገበያ ግን  እስከ 27 ብር በመመንዘር ላይ ነው።