ለህውሃት 40ኛ አመት መታሰቢያ ድግስ  ከባለሀብቶች ብቻ 45 ሚልየን ብር ተገኘቷል፡፡

ጥር ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ(ህወሀት)  ጽ/ቤት በተሰጠው መግለጫ  እንደተመለከተው፤ የካቲት 11 ለሚከበረው የድርጅቱ 40ኛ ዓመት በዓል ማክበሪያ   ከባለሀብቱ ብቻ  45 ሚልዩን ብር  ስፖንሰር ተገኝቷል፡፡

በመግለጫው በመቀሌ ከፍተኛ ተራራ ላይ የመለስን  ምስል የያዘ ባለሁት አውታር  ሐውልት እየተገነባ እንደሆነ የተጠቀሰ ሲሆን፤  የዚህም ወጪ  ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ አና ከገጠር መንገዶች ተቋራጭ ድርጅት ይሸፈናል ተብሏል፡፡

እስካሁን በአዲስ አበባ ካሉ ባለሃብቶች ፤አሰመጭ እና ላኪ ድርጅት ባለፀጎች ለድርጅቱ  40ኛ አመት የመሰተንግዶ ወጭ  23 ሚልዩን ብር መሰብሰቡም ተገልጿል። ይህ ለህወሀት 40ኛ ዓመት በዓል  መስተንግዶ ቃል የተገባውና የተሰበሰበው ገንዘብ፤ ከመንግስት ተቋማትና ከሌሎች ድርጅቶች ይሚሰባሰበውን ሳይጨምር ነው።