መስከረም ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በየካ እና በንፋስ ስልክ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጡት ቤታቸው የፈረሰባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች አሁንም መጠጊያ አጥተው እየተሰቃዩ ነው።
በየካ አካባቢ የሚኖሩ አንድ ግለሰብ ለኢሳት እንደገለጡት ህጻናት፣ አሮጊቶችና ሽማግሌዎች አሁንም መጠለያ አጥተው ቢቸገሩም መንግስት ግን ለችግራቸው መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።
መሀንዲሶች ህጋዊ ነው ብለው በማጽደቃቸው ገንዘባቸውን አፍስሰው መሰረተ ልማቶችን መስራታቸውን ነዋሪዎች ይናገራሉ ። አቶ አዱኛ
ቤታቸው የሚፈርስባቸው ሰዎች የመንግስትን እርምጃ በመቃወማቸው ድብደባ እንደተፈጸመባቸው አቶ ይድነቃቸው የተባሉ ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰው ተናግረዋል
በትናንትናው እለት ከ60 በላይ የሚሆኑ ቤቶች መፍረሳቸውን አቶ ይድነቃቸው ተናግረዋል ።