መጋቢት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ እንደጠቀሰው የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት እና የሽግግሩ መንግስት ደጋፊ ታጣቂዎች ፣ የአልሸባብ ደጋፊዎች ይሆናሉ ብለው የጠረጡዋቸውን ሰዎች በጅምላ ይገድላሉ፣ ይደበድባሉ፣ ያስራሉ ሲሉ ጠቅሷል።
ሂውማን ራይተስ ወች እንደሚለው በባይደዋና በበለተወይም መምህራን ሳይቀሩ ተገድለው ተገኝተዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አልሸባብ በደፈጣ ውጊያ ወይም ፈንጆችን በማጥመድ በኢትዮጵያ ሰራዊት አባላትና በሶማሊያ መንግስት ደጋፊ ታጣቂዎች ላይ የሚፈጽመው ጥቃት መጨመር፣ በእነዚህ አካባቢዎች በሚኖሩ ነዋሪዎች ላይ የሚወሰደው የአጸፋ እርምጃ እንዲጨምር አድርጎታል።
አንድ የበለደውይን ተወላጅ እንዳለው በአልሸባብ ጊዜ እንደምትገደል ስለምታውቅ ጥንቃቄ ታደርገለህ፣ አሁን ማንም ታጣቂ መጥቶ ሊደፋህ ይችላል ብሎአል።
የኢትዮጵያ ጦር አካባቢውን ከተቆጣጠረ በሁዋላ ሁኔታው ይሻሻላል ብለው ቢጠብቁም፣ እየባሰ እንጅ እየተሻሻለ አለመምጣቱን ነዋሪዎች መግለጣቻውን ሂውማን ራይተስ ወች ገልጧል።
የሂውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር የሖኑት ሌስሌ ለፍኮው ፣ በጦርነት ወቅት የሚፈጸም ጅምላ ግድያ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
ሂውማን ራይትስ ወች እኤአ በ2006 የኢትዮጵያ መንግስት ሶማሊያን በወረረበት ወቅት የጦር ወንጀል መፈጸሙን የሚገልጥ ሪፖርት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide