ኢሳት (ግንቦት 22 ፥ 2009)
የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሃይሎችን እና የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸውን በማስተባበር ሁሉንም አሳታፊ የሆነ ብሄራዊ ምክር ቤት ለመመስረት ስምምነት መደረጉን በሲያትል የተካሄደው ጉባዔ የአቋም መግለጫ አመለከተ።
በአቋም መግለጫው እንደተመለከተው በኢትዮጵያ የተካሄውን ህዝባዊ እምቢተኝነት የበለጠ ማጠናከር ያልተቻለው ጠንካራ የተቃዋሚ ሃይሎች ህብረት ባለመኖሩ ነው።
ስለሆነም፣ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመፍጠር በሽግግርነት ሁሉን አሳታፊ ብሄራዊ ምክር ቤት ማቋቋም ማስፈለጉን በጉባዔው ስምምነት ላይ ተደርሷል።
ለዚህም በጉዳዩ ላይ ጥናት የሚያደርግ ሰባት አባላት ያሉት ኮሚቴ መመስረቱ ይፋ ተደርጓል።