ሁለት የእርዳታ ሠራተኞች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 13/2010)

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሁለት የዕርዳታ ሠራተኞች ተገደሉ።

የፈረንሣይ መንግሥታዊ ያለሆነ ተቋም ሃይድሮሊክ ሣን ፍሮንቴይር ባልደረባ የነበሩት ሀለቱ ግለሠቦች የተገደሉት ባለፈው ቅጻሜ መሆኑ ታውቋል።

የገዳዮቹ ማንነት እስካሁን አልታወቀም።

በምሥራቃዊ የኮንጎ ኪቩ በተባለው ግዛት የተገደሉት ሁለቱ የዕርዳታ ድርጅት ሰራተኞች በስምና በዜግነት አለመገለፃቸውን ከቢቢሲ ዘገባ መረዳት ተችሏል፡፡

በከፍተኛ የፖለቲካ ውጥረት ውስጥ በምትገኘው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በአንድ ዓመት ግዜ ውስጥ የተገደሉት የዓለም አቀፍ ዕርዳታ ድርጅት ሠራተኞት ቁጥር 4 ደርሧል።

ከፈረንሳዩ ሃይድሮሊክስ ሣንፍሮንቴር ሠራተኞች በፊት ሁለት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤክስፐርቶች ተገድለዋል ::

ለ32 ዓመታት በአምባገነኑ ሞቡቱ ሴሴኮ አገዛዝ ሥር የቆየችው የቀድሞዋ ዛየር የዛሬዋ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ላለፉት 21 ዓመታት ደግሞ በአባትና ልጅ በሎረን ካቢላ እና ጆሴፍ ካቢላ አገዛዝ ውስጥ ትገኛለች፡፡

የአባታቸውን መገደል ተከትሎ ሥልጣን የያዙት ጆሴፍ ካቢላ የሥልጣን ዘመናቸውን ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ ለማራዘም የሚያደርጉት ጥረት በዛች ሃገር ቀውስን አስከትሏል፡፡