ጄኔራልነት አብርሃ ወልደማርያም በጡረታ መሰናበታቸው ተረጋገጠ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 6/2010) በቅርቡ የሙሉ ጄኔራልነት ማዕረግ ከተሰጣቸው የጦር አዛዦች አንዱ አብርሃ ወልደማርያም በጡረታ መሰናበታቸው ተረጋገጠ።

ኢሳት ባገኘው መረጃ መሰረት ጄኔራል አብርሃ ወልደማርያም ከሰኞ ሰኔ 25/2010 ጀምሮ ከሰራዊቱ በጡረታ ተሰናብተዋል።

ጄኔራል አብርሃ ወልደማርያም ለረጅም አመታት የምስራቅ እዝ አዛዥ ሆነው በሶማሌ ክልል ጉዳይ ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ሲያደርጉ መቆየታቸውም ይነገራል።

ጄኔራሉ በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ በከፍተኛ የኮንትሮባንድ ንግድ የከበሩና እጅግ የተንደላቀቀ ዘመናዊ መኖሪያ በአዲስ አበባ ከተማ ከገነቡ የሕወሃት የጦር ጄኔራሎች አንዱ መሆናቸውም ተመልክቷል።

በቅርቡ የጄኔራልነት ማዕረግ ተሰጥቷቸው በምክትል ኢታማጆር ሹምነት ተሰይመው ከነበሩት አራት ጄኔራሎች አንዱ የሆኑት አብርሃ ወልደማርያም ከሰኔ 25/2010 ጀምሮ ከሰራዊት በጡረታ ተሰናብተዋል።