የአዴሃን ሃይሎች ወደ አገራቸው ገቡ

የአዴሃን ሃይሎች ወደ አገራቸው ገቡ
( ኢሳት ዜና ጳግሜን 05 ቀን 2010 ዓ/ም ) የህወሃትን አገዛዝ በመቃወም የትጥቅ ትግል ሲያካሂዱ የቆዩ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች ንቅናቄ አመራሮችና የሰራዊ አባላት ወደ አገራቸው ገብተዋል። የሰራዊቱ አባላት ወደ አገር ሲገቡ የጎንደርና የሌሎችም ከተሞች ነዋሪዎች በመንገዱ ላይ በመውጣት የጀግና አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አዴሃን ከመንግስት ጋር ከተነጋገረ በሁዋላ ወደ አገር ቤት የገባ ሲሆን፣ የድርጅቱ አመራሮች በሰላማዊ መንገድ ትግላቸውን ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አዴሃን በአማራ ህዝብ ላይ የሚደረሰውን ጭቆና በሃይል ታግሎ ለማስወገድ በመደራጀት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል።