የሰላም እና የአስተዳደር ኮሚሽኖችን ለማቋቋም የተረቀቀ አዋጅ ቀረበ

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 20/2011) የሰላም እና የአስተዳደር  ወሰንን የተመለከቱ ኮሚሽኖችን ለማቋቋም የተረቀቀ አዋጅ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።

በኢትዮጵያ  ከተፈጸሙ ወንጀሎች ጋር  ተያይዞ ሲንከባለሉ  የመጡ ጉዳዮችን በዘላቂነት በዕርቅ ለመቋጨት  የሚቋቋመውን የዕርቅ ኮሚሽን ምክር ቤቱ ከተወያየበት በኋላ ለሚመለከተው የፓርላማው አካል ለዝርዝር ዕይታ መምራቱ ተመልክቷል።

 

የአስተዳደር ወሰን እና ማንነትን በተመለከተ የሚነሱ ጥያቄዎችን እንዲሁም የሚቋቋመውን ኮሚሽን በተመለከትም ምክር ቤቱ ተወያይቶበታል።–ለዝርዝር ዕይታ እንደመራውም መረዳት ተችሏል።

 

ይህ ኮሚሽን በኢትዮጵያ ከማንነት እና ከአስተዳደር አካባቢዎች ጋር ተያይዞ የተከሰቱ አለመግባባቶችን በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ጥናት በማድረግ ይመልሰዋል ተብሎ ይጠበቃል።