የመስቃን ቤተ ጉራጌዎችንና የማረቆ ብሄረሰብ አባላትን ለማጋጨት በተደረገ ጥረት የበርካታ ዜጎች ህይወት አለፈ

የመስቃን ቤተ ጉራጌዎችንና የማረቆ ብሄረሰብ አባላትን ለማጋጨት በተደረገ ጥረት የበርካታ ዜጎች ህይወት አለፈ
( ኢሳት ዜና መስከረም 08 ቀን 2011 ዓ/ም ) መስከረም 3 ቀን 2011 ዓም የወረዳ የካቢኔ አባላት ምርጫን ተከትሎ በምርጫው የተከፉ ወገኖች የማረቆን ብሄረሰብና የመስቃን ጉራጌ ብሄረሰቦችን አነሳስተው በፈጠሩት ግጭት ከሁለቱም ወገን ከ30 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ግጭቱን ለማብረድ የፌደራል ፖሊስ ጣልቃ የገባ ሲሆን፣ የጦር መሳሪያ በታጠቁት እና ለግጭቱ መንስዔ ሆነዋል በተባሉት ግለሰቦች ላይ በወሰደው እርምጃ በርካታ ዜጎች ተገድለዋል።
በአካባቢው አንጻራዊ መረጋጋት የታየ ቢሆንም፣ ውጥረቱ ግን አሁንም እንዳለ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።