ኦህዴድ ነባር አመራሮችን አሰናበተ

ኦህዴድ ነባር አመራሮችን አሰናበተ
( ኢሳት ዜና መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ/ም ) የኦህዴድ መስራቾችና የህወሃት ደጋፊዎች ተደርገው የሚቆጠሩት አቶ አባዱላ ገመዳ፣ ጌታቸው በዳኔ፣ ኩማ ደመቅሳ፣ ግርማ ብሩ፣ እሸቱ ደሴ፣ ተፈሪ ጥያሩ፣ ደግፌ ቡላ፣ አበራ ሃይሉ፣ ሱሌይማን ደደፎ፣ ኢተፋ ቶላ፣ ዳኛቸው ሽፈራውና ጊፍቲ አባሲያ ከድርጅቱ ተሰናብተዋል። ፓርቲው ራሱን ከኦህዴድ ወደ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ወይም ኦዴፓ ቀይሯል። በጅማ እየተካሄደ ባለው የድርጅቱ ጉባኤ ላይ ሊቀመንበሩ ዶ/ር አብይ አህመድ ቀን ቀን ከድርጅቱ ማታ ማታ ደግሞ ከጠላቶች ጋር አብረው የሚውሉ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስጠንቅቀው ነበር።