ኦህዴድ ስያሜውን ቀየረ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 10/2011)ኦህዴድ ስያሜውን መቀየሩና ከ10 በላይ የሚሆኑ ነባር የፓርቲውን አባላት በክብር ማሰናበቱ ተገለጸ።

በጅማ እየተካሄደ ባለው 9ኛ የድርጅቱ ጉባኤ ላይ ኦህዴድ ስያሜውን በመቀየር የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ተብሏል።

ፓርቲው ከነባር የፓርቲው አባላት አቶ አባዱላ ገመዳን ጨምሮ ከ10 በላይ የሚሆኑ አባላቱን በክብር አሰናብቷል።

ከነዚህም ውስጥ አቶ ሱለይማን ደደፎ ፣አቶ ድሪባ ኩማ ፣አቶ ጌታቸው በዳኔ፣ አቶ ግርማ ብሩ፣ አቶ ኩማ ደመቅሳ፣ አቶ ሽፈራው ጃርሶ፣ አቶ ደግፌ ቡላ፣ አቶ አበራ ኃይሉ ፣ አቶ ተፈሪ ጥያሩ፣ አቶ ኢተፋ ቶላ፣ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው ፣ወ/ሮ ጊፍቲ አባሲያ ና አቶ እሸቱ ደሴ ይገኙበታል።

ፓርቲው  ለጉባኤተኛው ባቀረበው አዲሱ ረቂቅ አርማ ላይም መጠነኛ የማሻሻያ ሀሳብ በማድረግ አጽድቋል ሲሉ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባሉ አቶ አዲሱ አረጋ ተናግረዋል፡፡