አዲስ አበባችን ማህበራዊ ንቅናቄ በይፋ ስራ ጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 18/2011)አዲስ አበባችን ማህበራዊ ንቅናቄ በይፋ መመስረቱንና ስራ መጀመሩን አስታወቀ።

ንቅናቄው ወደ ስራ ሲገባም የአዲስ አበባ ህዝብ መሰረታዊ ችግሮች ምንድን ናቸው የሚሉትን ሃሳቦች መሰረት በማድረግ ነው ይላሉ የንቅናቄው ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት አቶ ሱራፌል ዘውዱ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ

አዲስ አበባችን ማህበራዊ ንቅናቄን ለመመስረት አራት ወራትን ፈጅቷል ይላሉ የንቅናቄው ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት አቶ ሱራፌል ዘውዱ።

በነዚህ ጊዜያት ውስጥና ከዛም ቀደም ብሎ ንቅናቄው በአዲስ አበባ ያሉትንና መሰረታዊ የሚባሉ ችግሮችን ሲያጠና ቆይቷል።

ንቅናቄው ሲመሰረትም በዋናነት የአዲስ አበበ ህዝብ መሰረታዊ የሚባሉ ፍላላጎቶችን መሰረት አድርጎ ነው

የአዲስ አበባ ጉዳይ በንቅናቄው እምነት የነዋሪዎቿ ነው ይላሉ አቶ ሱራፌል።

የአዲስ አበባ ነዋሪ እስካሁን የመረጠው የራሱ የሆነ መሪ የለውም።ንቅናቄውም በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ነው ጊዜያዊ ፕሬዝዳንቱ የተናገሩት።

እንደ አቶ ሱራፌል አባባል ንቅናቄው ቅድመ እውቅና ተሰቶት ስራውን ጀምሯል።አባላትን የማደራጀት ስራም ቀጣይ የንቅናቄው አጀንዳ ነው።

ማህበሩ በቀጣይም አቅሙን አጠናክሮ የጀመረውን አላማ ከግብ ለማድረስ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከጎኑ እንዲቆሙለት ጥሪውን አቅርቧል።