በጅግጅጋ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ንብረታቸው የወደመባቸው ባለሃብቶች የካሳ ጥያቄያቸው እስካሁን መልስ አለማግኘታቸውን ገለጹ

በጅግጅጋ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ንብረታቸው የወደመባቸው ባለሃብቶች የካሳ ጥያቄያቸው እስካሁን መልስ አለማግኘታቸውን ገለጹ
( ኢሳት ዜና መስከረም 29 ቀን 2011 ዓ/ም ) ከ300 በላይ የሚሆኑትና በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ አሌ እንደመሩት በሚታመነው ግጭት ንብረታቸው የወደመባቸው የከተማዋ ነጋዴዎች፣ በአጠቃላይ ከ700 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ካሳ ከመንግስት ይጠብቃሉ። መንግስት ካሳ ለመስጠት ፈቃደኛ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ መልስ ባለማግኘታቸው ለከፍተኛ ችግር መደረጋቸውን ነጋዴዎች ገልጸዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ አዲስ የተቋቋመውን የክልሉን አስተዳደር ባለስልጣናት ለማናገር ብንሞክርም አልተሳካልንም።