በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጣናን ለመታደግ ማሽን ገዝተው ወደ አገር ቤት ላኩ

በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጣናን ለመታደግ ማሽን ገዝተው ወደ አገር ቤት ላኩ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) ጣና ሃይቅን ከእንቦጭ አረም ወረራ ለመታደግ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን 2 ዘመናዊ ማሽኖችን ገዝተው መላካቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። ሁለቱ ማሽኖች ካናዳ ከሚገኝ ማሽን አምራች ድርጅት በ92 ሺ 350 የአሜሪካ ዶላር መገዛታቸውን፣ ተጨማሪ ማሽኖችን ለመግዛትም ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ ጋር የመስክ ጥናት እያካሄዱ መሆኑን አዘጋጆች ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም የተላከው ማሽን በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ጂቡቲ ወደብ ይደርሳል ብለው እንደሚጠብቁ ጣናን ለመታደግ የተቋቋመው ግብረሃይል አስታውቋል።