በወልቃይት ህዝብ ላይ ጦርነት ያወጀ የሚመስል ነገር ተሰርቷል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 17/2011) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም የማንነት ጥያቄን በሚመለከት የሰጡት መግለጫ በወለቃይት ህዝብ ላይ ጦርነት የማወጅ ያህል ነው ሲሉ ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ ለኢሳት ተናገሩ።

ጥያቄያችን የረጅም ዓመታት ጥያቄ ነው ያሉት  ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ህጉን ተከትለን የማንነት ጥያቄያችንን ካቀረብን  ከሶስት ዓመታት በላይ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በመሆኑም ወይዘሮ ኬሪያ የህወሃት ስራ አስፈጻሚ ሆነው ሳለ ጥያቄያችን መልስ ሊያገኝ ስለማይችል እሳቸው በቦታው እስካሉ ድረስ ምንም ዓይነት ጉዳይ ይዘን አንሄድም ብለዋል።

ከዚህ በኋላ ይህ ጥያቄ የአማራ ህዝብ ጥያቄ በመሆኑ ጉዳዩን ህዝቡ ይወስናል ሲሉም ተናግረዋል።