ለቡራዪ ተፈናቃዮች በ72 ሰዓት ውስጥ ከ265 ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 10/2011) በአርቲስት ታማኝ በየነ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ በዓለም ዓቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት በተከፈተ የጎ ፈንድ ሚ የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ ለቡራዪ ተፈናቃዮች በ72 ሰአት ውስጥ ወደ ከ265ሺህ ዶላር የሚጠራ ገንዘብ ተሰበሰበ።

አዘጋጆቹ እስከ 500ሺህ ዶላር ለመሰብሰብ ማቀዳቸውን በመግለጽ ኢትዮጵያውያን ለወገናቸው ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ጥሪ አድርገዋል።

በተያያዘ ዜና ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ከቡራዩ ለተፈናቀሉ ዜጎች አንድ ሚሊየን ብር መስጠቱ ታውቋል።

ቴዲ አፍሮ ከቤተሰቡና ከስራ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን ዛሬ ተፈናቃዮቹን መጎብኘቱንም የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

የተፈጸመው ድርጊት ከኢትዮጵያዊነት ባህል የዘለለ ከሰው ልጅ የሞራል ህግም ያፈነገጠ ነው በማለት ሀዘኑን ገልጿል።