ጋዜጠኛ ተመስጌን ደሳለኝ ያለበትን አድራሻ ማወቅ አለመቻላቸውን ቤተሰቦቹ ገለጹ

ኅዳር ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ይገኝ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስጌን ደሳለኝ ቤተሰቦቹ  ወደታሰረበት ዝዋይ እስር ቢሄዱም ሊገኙት አልቻሉም።

በሳምንት ሁለት ቀናት ሀሙስ እና እሁድ በቤተሰቦቹ ብቻ እንዲጎበኝ የተፈቀደለት ጋዜጠኛ ተመስጌን ፣ ከህዳር 28 ቀን 2009 ዓ.ም በኋላ ግን ሊጎበኙት የሄዱት ቤተሰቦቹ ሊያገኙት አልቻሉም።  ቤተሰቦቹ መግባት እንደማይችሉ በጥበቃ ሰራተኞች የተነገራቸው ሲሆን፣   አድራሻውን ለማወቅ ወደ ቂሊንጦ እና ማእከላዊ እስር ቤት ቢሄዱም ”ያለበትን አናውቅም” የሚል ተመሳሳይ ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

ጋዜጠኛ ተመስገን በቅርቡ የአመክሮ ጊዜውን ጨርሶ ይፈታል ተብሎ ቢጠበቅም፣   የአመክሮ መብቱን ተነፍጓል። ጋዜጠኛ ተመስጌን ደሳለኝ ያለበት አድራሻ አለመታወቁን ተከትሎ ቤተሰቦቹ  እና ጓደኞቹ ከፍተኛ ስጋት ላይ መወደቃቸውም ታውቋል።