የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሶማሊያን ጎበኙ

ጥር 24 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፣ ዊሊያም ሄግ የሶማሊያ ዋና ከተማ በሆነቸው ሞቃዲሾ የተገኙት  በከፍተኛ ወታደራዊ አጀብ ነው።

የአፍሪካ ህብረት አባል አገሮች በሶማሊያ መረጋጋት እንዲፈጠር ጦራቸውን እንዲልኩ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

ከሁለት ሳምንት በሁዋላ እንግሊዝ በሶማሊያ ጉዳይ የሚመክር አንድ አለማቀፍ ውይይት አዘጋጅታለች። በውይይቱ ላይ አቶ መለስ ዜናዊ ስለመገኘታቸው የተነገረ ነገር ባይኖርም የኢትዮጵያ፣ የሶማሊያ እና የኬንያ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉብኝት በሶማሊያ አንጻራዊ የሆነ ሰላም እየሰፈነ እና የአልሸባብ ጥንካሬ እየቀነሰ መምጣቱን ያሳያል በማለት የፖለቲካ ተንታኞች እየተናገሩ ነው።

አልሸባብ አብዛኛውን የሶማሊያ ደቡባዊ ክልል ተቆጣጥሮ ይገኛል። የኢትዮጵያ ጦር በለደወይን ተብላ የምትጠራውን ከተማ ከአልሸባብበ እጅ መልሶ ማስለቀቁ ይታወቃል። ጦሩ በአልሸባብ ላይ ተጨማሪ ጥቃት ለመፈጸምም በዝግጅት ላይ ነው።