የኢትዮጵያ ፓርላማ ከ320 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ

(ኢሳት ዜና – ሰኔ 30 2009)

የኢትዮጵያ ፓርላማ 1/3ኛ የበጀት ጉድልት ያልበትን ከ320 ቢሊዮን ብር በላይ አመታዊ በጀት አጸ።

የ100 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት ያለበት የመንግስት አመታዊ በጀት ከብድር እና እርዳታ ይሸፈናል ጠብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል ።

ዋናው ገቢ ግን ከግብር እና ከሃገር ውስጥ የሚሰበሰብ ነው ተብሏል።

ይህ በጀት ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ 17 በመቶ ብልጫ ያለው ቢሆንም የበጀት ጉድለቱ ግን የአጠቃላይ መጠኑ 1/3ኛ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ።

ከካፒታል በጀት ከ114 ቢሊዮን ብር በላይ ሲመደብ ለአጠቃላይ የወጪ በጀት ደግሞ 81.8 ቢሊዮን ብር ተመድቧል ።የ100 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት ያለበት የመንግስት አመታዊ በጀት ከብድር እና እርዳታ ይገኛል ጠብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል ።ዋናው ገቢ ግን ከግብርና ከሃገር ውስጥ የሚሰበሰብ ነው ተብሏል ።በበጀት እቅዱ ላይ የቀረበው መረጃ እንደሚያመለክተው ለልማት የሚውለው ገንዘብ ሲቀንስ ለመከላከያና ለጦር መሳሪያ የሚወጣው ግን ጨምሯል ።በዚሁም መሰረት የመከላከያ በጀቱ አምና 11 ቢሊዮን ብር ያህል  የነበረው በዘንድሮው በጀት ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲሆን ተደርጓል ።የልማት ፕሮጀክት በጀቱ ደግሞ አምና 12 ቢሊዮን የነበረው ዘንድሮ ወደ 7 ቢሊዮን ብር እንዲወርድ ተደርጓል ተብሏል ።  ኢትዮጵያ ያለባት የብድር ጫና ከ5 መቶ ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱና ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ35 ቢሊዮን ብር መጨመሩ መገለጹ ይታወሳል ። ከውጭ ንግድ ገቢ ኢትዮጵያ የምታገኘው ገቢ ደግሞ ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ5 ቢሊዮን ቀንሷል ። ከፍተኛ የገንዘብ ግሽበት ባለባት ኢትዮጵያ የእዳ ጫናውና የውጪ ምንዛሪ እጥረት በሃገሪቱ የኢኮኖሚ ሁኔታ ላይ ችግር እየፈጠረ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ ።   

ይህ በእንዲህ እንዳለም የትግራይ ክልል ምክር ቤት ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ማጽደቁ ተነግሯል ። የኢትዮጵያ በጀት ከ320 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኖ ቢጸድቅም የበጀት ጉድለቱ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑ ብድር ወይም እርዳታ ባይገኝ እንዴት ይሸፈናል የሚለው ግልጽ አይደለም ። ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር መንግስት ከብሄራዊ ባንክ ሲበደር መቆየቱ ቢታወቅም ይህ አሰራር በኢኮኖሚው ላይ ችግር በማስከተሉ እንዲቀር መደረጉ ይነገራል ።