የአቶ አግባው ሰጠኝ ህይወት አደጋ ላይ መውደቁ ተሰማ

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 10/2009)የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሰሜን ጎንደር አስተባባሪ አቶ አግባው ሰጠኝ ህይወቱ አደጋ ላይ መውደቁን አስታወቀ።
ጎንደር ኮሽ ባለ ቁጥር ስቃይና ሰቆቃ ይፈጸምብኛል በሚል ለፍርድ ቤት የገለጸው አቶ አግባው ሰጠኝ፡ በህይወት ስለመቆየቴም ዋስትና የለኝም በማለት መናገሩ ተሰምቷል።
ማረሚያ ቤቱ ፡አቶ አግባው እስረኞችን በማሳመጽና መሳሪያ ከጠባቂዎች ለመንጠቅ በመሞከር ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ ነው በማለት ምላሽ ሰጥቷል።
የመብት ተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያን በአቶ አግባው ሰጠኝ ላይ እየደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመቃወም በማህበራዊ ሚዲያዎች ዘመቻ ከፍተዋል።
በሌላ በኩል በቅርቡ ከእስር የተለቀቀው የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ የግድያ ዛቻ እየተሰነዘረበት መሆኑ ታውቋል።
በደህንነቶች ክትትል እየተደረገበት መሆኑንም የደረሰን መረጃ አመልክቷል።