የአምቦና የወሊሶ ነዋሪዎች የጀመሩት አድማ ወደ ታሪካዊቷ ጊንጪና ጉደር መሻገሩ ታወቀ

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 2/2009) የወህኒ ቤት ሃላፊዎች በዶክተር መራራ ላይ የሚፈጽሙት ኢሰብአዊ ድርጊት ያስቆጣቸው የአምቦና የወሊሶ ነዋሪዎች የጀመሩት አድማ ወደ ታሪካዊቷ ጊንጪና ጉደር መሻገሩ ታወቀ።
የኦሮሚያ ክልላዊ አመጽ በህዳር 2008 የተቀሰቀሰባት ጊንጪ ዛሬ ማክሰኞ ነሀሴ 2/2009 አድማውን መቀላቀሏ ይፋ ሆኗል።
ዶክተር መራራ ጉዲናን ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እንዲሁም በነጋዴዎች ላይ የተጣለው ከፍተኛ ግብር እንዲነሳ በመጠየቅ የተጀመረው አድማ በአምቦ ለሁለተኛ ጊዜ ሲቀጥል በተመሳሳይ መስመር ላይ ያሉት ጊንጪና ጉደር ዛሬ አድማውን ተቀላቅለዋል።