ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ዝምባብዌ የእርሻ ማሳ ውስጥ ተደብቀው ተገኙ

ታኅሣሥ ፳፰ (ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- በዝንባቢዌ ማሮንዴራ ግዛት ውስጥ ቁጥራቸው 34 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በእርሻ ማሳ ውስጥ ተደብቀው ተይዘዋል።

ስደተኞቹ የአገሪቷን ሕግ ተላልፈው በሕገወጥ መንገድ መግባታቸውን ተከትሎ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ስደተኞች በሙሉ ወንዶች ሲሆኑ ከመሃከላቸው እድሜያቸው ከ11 እስከ 12 የሚገመቱ አራት ታዳጊዎችም ይገኙበታል።

ስደተኞች ከአንዱ በስተቀር ሌሎቹ የቋንቋ ችግር ያለባቸው ሲሆን በኢንባሲያቸው በኩል አስተርጓሚ እስኪቀርብላቸው ድረስ በእስር ላይ ይቆያሉ።የ ክስ ዝርዝሩ ላይ እንደሰፈረው ስደተኞቹ ባለፈው ዓመት እ.ኤ.አ. ዲሴንበር 16 ቀን 2016 በሙቱኮ በኩል አድርገው ማሮንዴራ የገቡ ሲሆን ከፊሎቹ ደግሞ በቺሌንቴ ኒያንዶሮ አድርገው በጊፍቲ ቤሬ መስመር በኩል ገብተዋል።

የአገሪቱ ፖሊስ ማሳውን በእሳት በማቃጠል በቁጥጥር ስር ያዋላቸው መሆኑንና  ከመሃከላቸው ምንም ዓይነት ሕጋዊ የጉዞ ሰነድ የያዘ አንድም ስደተኛ አለመኖሩን ኒውስ ዴይ ዘግቧል።