“አሁን ያለው የ ኢኮኖሚ ዕድገት፤ የቤተ-መንግስት እድገት ነው”ሲሉ ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ ገለጹ

ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በመመስረት ላይ ያለውን የሰማያዊ ፓርቲ በ አባልነት የተቀላቀሉት ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ ይህን ያሉት፤ ከሳምንታዊው ሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ላይ ነው።

እርስዎ እንደ አንድ ምሁር በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ምን አስተዋፅኦ አደርጋለሁ ብለው ነው ወደ ፖለቲካ የሚገቡት?
ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ፡- ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ለመስራት ስወስን ትልቁ ተልዕኮዬ ፓርቲውን በሰው ኃይል፣ በአመለካከትና በአሰራር ወደተሻለ ደረጃ በማድረስ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ኅብረት ፈጥረን የምንሰራበትን መንገድ ለማመቻቸት ነው። በተለይም የወጣቱን ኅብረተሰብ ክፍል እያገዝን ጠንካራ ተፎካካሪ ኃይል እንዲገነባ ለማድረግ ነው ዓላማ ያደረኩት።
ሰንደቅ፡- የፖለቲካ እምነትዎና አስተሳሰብዎ ምንድን ነው?”እርስዎ እንደ ምሁር በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ምን አስተዋጽኦ አደርጋለሁ ብለው ነው ወደ ፖለቲካው የገቡት?” ተብለው የተጠየቁት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ “ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ለመሥራት ስወስን ተልዕኮዬ ፓርቲውን በሰው ሀይል፣በ አመለካከት እና በ አሠራር  ወደተሻለ ደረጃ በማድረስ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ህበረት ፈጥረን የምንሠራበትን መንገድ  ማመቻቸት ነው” ብለዋል።

“በተለይ በአሁኑ ወቅት የምናራምደው ፖሊሲ ወጣ ገባ፣ የተዘበራረቀና በ ዕውቀት ላይ ያልተመሰረተ በመሆኑ ችግር ውስጥ ነን”ያሉት ፕሮፌሰር ዝናቡ፤በተለይ መሬትን በተመለከተ የምንከተለው ፖሊሲ ለቁልቁለቱ ጉዟችን ዋነኛው ምክንያት ነው ብለዋል።

መንግስት ተግባራዊ እያደረገ ያለው ፖሊሲ በ ኢኮኖሚ እንዳንጠነክር የሚያደርግ ነው ያሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ በኢኮኖሚው የተጠናከረ ሀይል በፖለቲካውም እየተጠናከረ እንደሚሄድ ስለሚታወቅ፤ መንግስት ያንን ለማሽመድመድ  ህብረተሰቡን የኢኮኖሚ አውታር ከሆነው  መሬት ጋር እየለያየው እንደሆነ አመልክተዋል።

ፕሮፌሰር ዝናቡ አክለውም፦”ህዝብ በፖለቲካ እንዳይጠነክር ስለሚለግ በኢኮኖሚ እንዲላሽቅ እየተደረገ ነው፤ ካቻምናን እና አምናን ሲያማርር የከረመው ህዝብ ዘንድሮ ደግሞ በከፋና በባሰ ሁኔታ ላይ ይገኛል። በዚህም ህዝቡ ተሰላችቷል። መሰላቸት ወዴት እንደሚያመራ ደግሞ ግልጽ ነው።ስለዚህ ከፖለቲካ አደረጃጀት አልፈን ኢኮኖሚውን የማናድን ከሆነ፤ከባድ ዋጋ እንከፍልበታለን”ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ሌላው ችግር የቋንቋ ፌዴራሊዝም እንደሆነ እና ፌዴራሊዝሙ ከይዘትም ባሻገር የቅርጽም ችግር እንዳለበት   ፕሮፌሰር ዝናቡ ጠቁመዋል።

“ የአንድ አገር ፌዴራሊዝም የ አገሪቱ የጋራ ታሪክ እንዳይኖር ካደረገ፤ ፌዴራሊዝም ሊባል እንደማይችል ያስረዱት ፕሮፌሰሩ፤”ህዝቡ የጋራ ማንነቱን ትቶ ወደ ግል ማንነቱ ከወረደ፤ በጋራ ማን ሊሆን ነው? የጋራ ማንነቱ የማይጎላ ህዝብስ በምን ሊጠራ ነው?”ሲሉ ጠይቀዋል።

የሚገርመኝ የመሪዎቻችን ጉዳይ ነው። መሪዎቻችን ወደ ስልጣን የሚመጡበትን መንገድ እንጂ ከስልጣን የሚወርዱበትን መንገድ አያውቁትም። አፄ ኃይለስላሴ ተራ ሰው ሆነው እንዴት ወደ ዘውዱ ሊመጡ እንደሚችሉ ጥሩ ስራ ሰርተዋል። መንግስቱም ወደ ቤተ-መንግስት የሚወስደውን መንገድ አውቆታል። መለስም እንዲሁ። ነገር ግን ሦስቱም ከቤተ-መንግስት እንዴት እንደሚወጡ አያውቁም። አፄ ኃይለስላሴ እዛው ቤተ-መንግስት ሲያዙ መንግስቱ አመለጠ። የዛሬውን ደግሞ አናውቅም። ስለዚህ መሪዎቻችን ወደቤተ-መንግስት የሚመጡበትን እንጂ የመውረጂያ ስትራቴጂ የላቸውም። ስለዚህ እኛ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የምንለው የእኛ መግቢያ መንገድ (ምርጫ) የእነሱ መውጪያ ይሆናል ነው የምንለው። ስለዚህ የምርጫ ስርዓት ማጠናከር በክብር ለመውረድና ለመውጣት”የሚገርመኝ የመሪዎቻችን ነገር ነው። መሪዎቻችን ወደ ስልጣን የሚወጡበትን እንጂ የሚወርዱበትን መንገድ አያውቁትም” ያሉት ምሁሩ፤ ዓፄ ሀይለሥላሴ ተራ ሰው ሆነው እንዴት ወደ ዘውድ ሊመጡ እንደሚችሉ ጥሩ ሥራ ሠርተዋል፤ መንግስቱም ወደ ቤተ-መንግስት የሚወስደውን መንገድ አውቆታል።መለስም እንዲሁ። ነገር ግን ሦስቱም እንዴት ከቤተ-መንግስት እንደሚወጡ አያውቁም’ ብለዋል።

ዓፄ ሀይለሥላሴ እዛው ቤተ መንግስት ውስጥ ሲያዙ መንግስቱ ማምለጡን ያወሱት ፕሮፌሰሩ፤ የዛሬውን ደግሞ አናውቅም ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

መሪዎቻችን ወደ ቤተ መንግስት የሚወጡበት መንገድ እንጂ መውረጃ ስትራቴጂ ባይኖራቸውም፤እኛ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የኛ መግቢያ መንገድ የነሱ መውጫ ይሆናል እንላለን  ሲሉም ተስፋቸውን ገልጸዋል።

ጋዳፊ፣ ቤን አሊ ፣ ሙባረክ እና ሌሎች መሰል አምባገነን ገዥዎች መግቢያውን ብቻ እንጂ መውጫውን መንገድ ባለማወቃቸው ምን እንደደረሰባቸው በመታየቱም  ስለ መውጫው መንገድ እናስብ”ሲሉ  ፕሮፌሰር ዝናቡ ምክራቸውን አስተላልፈዋል።

እንደ አንድ ኢኮኖሚ ምሁር በ አገሪቱ ያለውን የ ኢኮኖሚ ሁኔታ እንዴት እንደሚያዩት የተጠየቁት ፕሮፌሰሩ፤ቀደም ባለው ጊዜ  የ አንድ አገር ዕድገት ባጠቃላይ አገራዊ ምርት(ጂ.ዲ.ፒ) ይለካ እንደነበር በማስታወስና አሁን ግን ያ መለኪያ ተቀይሮ “ጠቅላላ የሀገሪቱ ደስታ” (ግሮውዝ ና ሽናል ሀፒነስ)ወደሚል መቀየሩን በመጥቀስ፤ ይህን ወደ እኛ አገር በማምጣት አብዘኣኛው ህዝባችን ደስተኛ ነው ወይ? ብለን ብንጠይቅ መልሱን እናገኘዋለን ብለዋል።

“11 እና  12 በመቶ አደግን የሚባለው የቁጥር ጨዋታ አይሠራም። ቻይና አገራችን መጥቶ ኢንቨስት እያደረገ ነው።በ እኛ  ኢኮኖሚ ውስጥ የገባውን የቻይና ገንዘብ ሁሉ እየቆጠርን አደግን እንላለን” ያሉት  ኢኮኖሚስቱ፤ “ በእርግጥ  አሁን ያለው  የኢኮኖሚ ዕድገት፤ የቤተ-መንግስት ዕድገት ነው” ሲሉ አጠቃለዋል።

__________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide