ባይዶዋን የተቆጣጠረው የኢትዮጵያ ሰራዊት ከተማዋን ለአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሀይል አስረክቦ ሊወጣ ነው ተባለ

ታህሳስ 27 ቀን 2004 ዓ/ ም

ኢሳት ዜና:-ቢቢሲ እንደዘገበው  የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ግዛት ለቆ እንዲወጣ የተወሰነው የአፍሪካ ህበረት የሰላምና የደህንነት ጉባኤ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነው።

የኢትዮጵያ ፣ የኬንያ ፣ የዩጋንዳ እና የብሩንዲ ጥምር ጦር ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አለው የሚባለውን አልሸባብን ለመውጋት በእየአቅጣጫው ዘመቻዎችን መክፈታቸው ይታወሳል።

የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱዌሊ ሙሀመድ በበለደወይን መገኘታቸውን ቢቢሲ አክሎ  ዘግቧል።

የኢትዮጵያን ጦር 5 ሲ የሚሆኑት የጅቡቲ ሀይሎች ይተኩታል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ  ጦር  ሶማሊያን በጊዜ ለቆ  የሚወጣው ከአራት አመት በፊት የደረሰበትን አይነት ሽንፈት በድጋሜ ላለመቀበል በመፈለግ ሊሆን  እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።