በኬንያ ናይሮቢ ስደት ላይ የነበረ ኢትዮጵያዊ  ታፍኖ መወሰዱን የኢሳት ምንጮች ገለጹ

ታኅሣሥ ፳፩ (ሃያ አንድ)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :-ምንጮቻችን የላኩት መረጃ  እንደሚያመለክተው በቅርብ ጊዜ ከኢትዮጵያ የመጣውና ላለፉት ሶስት ወራት በናይሮቢ በስደተኝነት የቆየው ስደተኛ  የመከላከያ ሰራዊት አባል የነበረ ሲሆን ፤ ምናልባትም ከፍ ያለ ማእረግ ሳይኖረው እንዳልቀረ ጠቁመዋል።

ይህ የመንግስት ሰው የነበረውና በቅርቡ ከሀገር ቤት ከድቶ የመጣው ስደተኛ ትናንት በናይሮቢ ዲዶራይ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር  ሳለ የኢትዮጵያ ደህንነቶች በፓትሮል  በመምጣት አፍነው እንደወሰዱት ምንጮቹ ገልጸዋል።

በኬንያና በኡጋንዳ  የፖለቲካ ስደተኞች የሆኑ በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚገኙ ቢሆንም፤ ሀገራቱ በግዛቶቻቸው ተገቢውን ጥበቃ ስለማያደርጉ፣ እንዲሁም የሀገራቱ ፖሊሶች በቀላሉ በሙስና ስለሚታለሉ ስደተኞቹ  በተደጋጋሚ  እየታፈኑ ሲወሰዱ ቆይተዋል።