በኦህዴድ ውስጥ የእርስ በርስ መጠላለፍና መወነጃጀል ተፈጥሯል

በኦህዴድ ውስጥ ያሉ የህወሓት ታማኞች ጓዶቻቸውን እያሳደዱና እያሰሩ ነው።
ሰኔ ፲፬( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦህዴድ ውሰጥ ያሉ ታማኝ የህወሓት አገልጋዮቸ አንፃራዊ በሆነ መንገድ የራስ መተማመንንበማዳበር ላይ ያሉትን የኦህዴድ አመራር አባላትን ማደን ጀምረዋል።
የህወኃት ተላላኪዎቹ-ጓደኞቻቸውን ኦህዴድ ውስጥ ሆነው ህገመንግሥቱን በኃይል ለማፍረስ ተንቀሳቅሰዋል ሲሉ ከሰዋቸዋል። ባለፉት 2 ቀናት የምስራቅ ሸዋና የአርሲ 3 የዞን አመራሮች የታሰሩ ሲሆን፤ አምስት ሹመኞች ደግሞ ከአገር ወጥተዋል።
ውጥረቱን ተከትሎ በበርካታ በኦሮሚያ የሚገኙ የዞን አመራሮች መኖሪያ ቤት በደህንነቶች ድንገተኛ ፍተሻ ተደርጓል።
ከመሣሪያ ግምጃ ቤት 78 ክላሽ መሳሪያ መጥፋቱ እየተነገረ ነው። በዚህም ምከንያት ኦህዴድ ውስጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ውጥረት መስፈኑ ታውቋል።