በአለፉት 6 ወራት ብቻ 325 ሰዎች እስር ቤት ህይወታቸው አልፏል

ሚያዝያ ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በ2009 ዓ.ም የስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ 325 በእስር ላይ የነበሩ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል። አሃዙ በቅሊንጦ እስር ቤት በእሳት የጋዩት እና በጥይት የተገደሉን እንዲሁም በብርሸለቆ እና በሰባት አሚት እስር ቤት በግፍ የተገደሉ እስረኞችን ያካተተ ነው። ይሁን እንጅ አሃዙ በየቀበሌው ያሉትን ጊዚያዊ እስር ቤቶችን መረጃ አላካተተም። ከ325 ሟች እስረኞች መካከል 49 ኙ በህክምና እጦት ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ በእሳት አደጋ ወይም በጥይት ህይወታቸውን ማጣታቸውን ከፌደራል ማረሚያ ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።