በታሪካዊነቱ የሚታወቀው ዋልድባ ገዳም ከመንግስት ጋር ውዝግብ ውስጥ ገባ

የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በአድርቃይ ወረዳ የሚገኘው የዋልድባ ገዳም አካባቢ ለሸንኮራ አገዳ ምርት ይፈለጋል በሚል ምክንያት መታጠሩ መነኮሳቱን ጨምሮ የአካባቢውን ህዝብ አስቆጥቷል።

በታሪካዊነቱ የሚታወቀው የዋልድባ ገዳም ከጥንት ጀምሮ በይዞታነት የያዘው መሬቱ በግድ እንዲታጠር መደረጉ ያበሳጫቸው መነኮሳትና ህዝቡ ከጠቅላይ ሚኒሰትሩ ጀምሮ ላሉ ባለስልጣናት አቤት ቢልም የሚሰማው አላገኘም።

ሰሞኑን ውዝግቡ እየተካረረ መምጣቱን፣ መንግስት ውሳኔውን ካላስተካካለ አላስፈላጊ የሆነ ግጭት ሊከሰት እንደሚችል የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

አካባቢው  ለሼክ አላሙዲን ይሰጣል የሚል ግምት መኖሩንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።