በስዊድን የኢሳት የድጋፍ ኮሚቴ የተሳካ ዝግጅት አካሄደ

የካቲት 20 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-እኤአ ፌብሩዋሪ 25፣ 2012 በስቶክሆልም በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 6 ሰአት እስከ ምሽ ቱ 4 ሰአት በተከናወነው በዚህ ዝግጅት የኢሳት ጋዜጠኞች የሆኑት ገሊላ መኮንንና አፈወርቅ አግደው፣ የአዲስ ነገር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው መስፍን ነጋሽ፣ በእንግድነት ተገኝተዋል።

ዝግጅቱ በክርስትናና እስልምና ሀይማኖት መሪዎች ጸሎት የተከፈተ ሲሆን በቅርቡ ለነጻነቱ ሲል ራሱን ያቃጠለውን የኔሰው ገብሬን በቅርብ የሚያውቁት መምህር ፍሰሀ ተሰማ የድጋፍ ኮሚቴውን በመወከል ንግግር አድርገዋል።

ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ የኢትዮጵያ ህዝብ ለምን ኢሳትን መደገፍ እንደሚገባው ሙያዊ ትንተና አቅርቧል።የኢትዮጵያ ወጣቶች ንቅናቄ የስዊድን ቻርተር ተወካይ ወጣት ደረጀ ሀብቴ ፣ ወጣቱ የተጣለበትን አገርን የማዳን ታላቅ አደራ እና የሚዲያን አስፈላጊነት በመዘርዘር ንግግር አድርጓል።

በዝግጅቱ መካከል ታዳሚዎች በታዋቂው ድምጻዊ ዳምጠው አየለ ወኔ ቀስቃሽ ሙዚቃ ሲዝናኑ እና አገራቸውን ሲያስታውሱ ውለዋል። በተጨማሪም የግጥምና  የተለያዩ  የኪነ ጥበብ ስራዎች ለህብረተሰቡ ቀርበዋል::

በእለቱ ለጫረታ የቀረበውን የየኔሰው ገብሬ ፎቶ ግራፍ  ብዙ ፍክክር ተደርጎበት አሸናፊው  ተረክቧል።  

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide