በህትመት ሚዲያዎች ላይ ያለው ጫና እየጨመረ ነው

ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በቅርቡ የሕትመት ሰታንዳርድ ውል ፈርሙ በሚል በአሳታሚዎች ላይ ጫና እያሳደረ

ያለው  የብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት በአሳታሚዎች ላይ ተዘዋዋሪ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው። ማተሚያ ቤቱ ባለፉት ሶስት ቀናት ሲ.ቲ.ፒ የተባለ ማሸን ( computer to

plate)ተበላሸቷል፣ፊልም የለኝም በማለት ጋዜጦችን በማጉላላት ላይ ከመገኘቱም በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት መታተም የነበረበት “ፍኖተ ነጻነት ” የተባለው የአንድነት ፓርቲ ጋዜጣ እንዳይታተም ምክንያት መሆኑ  ታውቋል፡፡በነገው ዕለት የሚወጡት “ሪፖርተር፣ሰንደቅ” የተባሉት  ጋዜጦች ፊልም ውጪ  እንዲያሰሩ አለበለዚያ መስተናገድ እንደማይችሉ ነግሯቸዋል፡፡የማተሚያ  ቤቱ ድርጊት ያልተለመደና አሳታሚዎችን ለተጨማሪ ወጪና መጉላላት የሚዳርግ ነው ተብሏል፡፡

የማተሚያ ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች ከአሳታሚዎች ጋር በውል ፈርሙ፣አንፈርምም ጉዳይ መወዛገብ ከጀመሩ በኃላ እንዲህ ዓይነት ነገር መምጣቱ ኃላፊዎቹ በፕሬሱ ላይ ቂማቸውን እየተወጡ ሳይሆን አይቀርም የሚል ዝንባሌ በብዙ አሳታሚዎች ዘንድ ተፈጥሯል፡፡

የአሳታሚዎቹ ኮሚቴ በዚህና ውል ፈርሙ በተባለው ጉዳይ ተወያይቶ ተጨማሪ አቋም ለመያዝ  በነገው ዕለት ቀጠሮ  የያዘ ሲሆን ከማተሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ጋር ለመጨረሻ ግዜ የፊታችን ዓርብ ዕለት ይወያያል  ተብሎ ይጠበቃል፡፡

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide