ሙስሊም ጋዜጠኞች አገር ጥለው ተሰደዱ

(Aug. 16) የመንግስት ጥቃት በመፍራት ከሀገር መሰደዳቸውን ሁለት የሙስሊሞች ጉዳይ ጉዳይ ጋዜጠኞች ይፋ አደረጉ። መንግስት ሁለቱን ጋዜጤኞች በቁም እስር ላይ አስቀምጧቸው እንደነበር ይታወሳል። ጋዜጠኛ ይስሐቅ እሸቱ እና አክመል ነጋሽ የተባሉት፤ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ወቅታዊ ጥያቄ አጉልቶ በማሳየት የሚታወቀው የሙስሊሞች ጉዳይ መጽሄት አዘጋጆች፤ መንግስት በሙስሊሙና በጋዜጠኞች ላይ የሚያደርሰውን ግፍ በመፍራት ከሐገር መሰደዳቸውን የጋዜጠኞቹን የቅርብ ሰዎች በመጥቀስ ፍኖተ ነጻነት ዘግቧል።
ጋዜጠኞቹ የሙስሊሞን እንቅስቃሴና መንግስት የሚፈጽምባቸውን ኢ-ፍትሐዊ እርምጃዎች ያጋለጡ በርካታ ጽሁፎች ማሳተማቸው ይታወቃል::
የኢትዮጵያ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ የሚያደርገውን የሐሰት ክስና ውንጀላ እንዲሁም እስራትና ፍርድን በተመለከተ የአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በጽኑ እየተቹት ቢሆንም ተግባሩን ቀጥሎበት ይገኛል።