መንግስት በሙስሊሞች ላይ የሚሰራውን ድራማ በሲዳማ ለመፈጸም እየተዘጋጀ ነው ተባለ::

ሐምሌ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም  

ኢሳት ዜና:- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የድምጻችን ይሰማ ተቃውሞውን ለማኮላሸት መንግስት በክፍለሀገራት የሚገኙ ሙስሊም የሆኑና ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችን ከየቦታው በማሰባሰብ እንቅስቃሴውን እንዲያወግዙ በማድረግና በቴሌቪዥን ቀርጾ በማቅረብ ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ስራ እየሰራ ሲሆን፣ ይህንኑ ስትራቴጂ በሲዳማ ላይ ለመድገም ዝግጅት ጀምሯል።

በሲዳማ የተነሳው ተቃውሞ በተለያዩ ጊዜዎች እያገረሸ በንጹህን ዜጎች እና በፌደራል ፖሊስ አባላት ህይወት ላይ ጉዳት እንዲደርስ አድርጓል።

ይህንኑ ተከትሎ የክልሉ መንግስት የፊታችን ማክሰኞ  የተወሰኑ ደጋፊዎችን አዋሳ በሚገኘው የባህል አዳራሽ በድብቅ በመጥራት፣ “የሲዳማን ችግር የሚፈጥሩት ጸረ ሰላም ሀይሎች ናቸው” የሚል ፕሮፓጋንዳ ለመስራት በዝግጅት ላይ ነው። በመንግስት ባለስልጣናት በጥንቃቄ የተመረጡ ከ1ሺ በላይ ሰዎች ጥሪ እንደተደረገላቸው ለማወቅ ተችሎአል።

ይህ ስትራቴጂ ህዝቡን ከሁለት በመክፈል  ጥያቄውን ለማዳፈን የታለመ መሆኑን የአካባቢው ሰዎች ይናገራሉ።

ካለፈው ወር ጀምሮ በዞኑ የሚታየውን አለመረጋጋት ስንዘግብ መቆየታችን ይታወሳል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide