አቶ ገብረመድህን አርአያ የዘማናችን አሉላ አባ ነጋ ተብለው በከፍተኛ ክብር ተሰየሙ

ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በምእራብ አውስትራሊያ በፐርዝ ከተማና አካባቢዋ ኗሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ጁን 23 ቀን 2013 ባደረጉት ልዩ ዝግጅት ታዋቂውን የነፃነት ተፋላሚና የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጅ አቶ ገብረመድህን አርአያን የዘመናችን አሉላ አባ ነጋ በማለት በክብር ሰየሙዋቸው። በዚህ ለእርሳቸው ታስቦ በተደረገው ልዩ የእራት ግብዣ ስነ ስርዓት ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን የተገኙ ሲሆን፣ እንግዶቹ ለአቶ ገብረመድህን አርአያ ...

Read More »

በቤተመንግስት ግቢ ዙሪያ አንድ ሰው ተገድሎ ተገኘ

ሰኔ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሀሙስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ጽህፈት ቤት ጀርባ  ሁለተኛው በር ከ150 እስከ 200 ሜትር  ባለ ርቀት ላይ አንድ ጎልማሳ አንገቱ ተቆርጦ  መገኘቱን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል።  – እማኞች እንደሚሉት  ሟቹ እድሜው ከ45 እስከ 53 የሚጠጋ ጸጉር አልባ ጎልማሳ ነው። የሟቹ የራስ ቅል  ባእታ ክሊኒክ አቅራቢያ ባለ አንድ ቦታ ላይ ተጥሎ ...

Read More »

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንቱ ስራ የሚ ለቁ ዳኞች ቁጥር መጨመሩን ተናገሩ

ሰኔ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ተገኔ ኔታነህ ሰሞኑን ለፓርላማ የመ/ቤታቸውን የ11 ወራት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት  ዳኞች በርካታ ችግሮች የተጋረጠባቸው በመሆኑ መስሪያቤቱን እየለቀቁ ነው ብለዋል። የዳኞች መኖሪያ ቤት ችግርን በዘለቄታነት ለመፍታት ሕንጻ ለመገንባት እየተደረገ ያለው ጥረት የተወሰነ መጓተት እንደሚታይበት ፕሬዚዳንቱ ጠቁመው እስከዚያ ድረስ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ መንግስት የኪራይ ቤት መስጠቱን እንዲቀጥል የተላለፈውን ...

Read More »

የግብርና ኢንቨስትመንትን የሚመራ ኤጀንሲ በመቋቋም ላይ ነው

ሰኔ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጽያ መንግስት የግብርናውን ኢንቨስትመንት የሚያደራጅና የሚመራ የግብርና መሬት አስተዳደር ኤጀንሲ በማቋቋም ላይ መሆኑ ተሰማ፡፡ አቶ ወንድይራድ ማንደፍሮ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ከመንግስት መገናኛ ብዙሃን ጋር ሰሞኑን ባደረጉት ቃለምልልስ በመንግስት በኩል የግብርናን ኢንቨስትመንት በማጠናከር ሰፋፊ የግብርና ልማቶች በአገሪቱ እንዲኖሩ መንግስት ፍላጎት እንዳለው በመጥቀስ ይህን የማጠናከር ስራ ለማከናወን አደረጃጀቱ እንዲስተካከል መደረጉን ገልጸዋል፡፡ የኤጀንሲው ማቋቋሚያ ...

Read More »

በአማራ ክልል የተከሰተው የተምች ወረርሺኝ በቁጥጥር ስር አልዋለም

ሰኔ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል በስምንት ዞኖች ከፍተኛ የሆነ የተምች ወረርሺኝ በመከሰቱ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡ ችግሩን ለመከላከል  እስካሁንም አጥጋቢ  እርምጃ አለመወሰዱን አርሶ አደሮች ይናገራሉ። ክልልሉ የግብርና ቢሮ የኤክስቴንሺን የስራ ሂደት ሃላፊ አቶ ላንተይደሩ ተስፋየ እንደተናገሩት በክልሉ በሚገኙ በ64 ወረዳዎች በ434 ቀበሌዎች የተከሰተው የተምች ወረርሺኝ በ62 ሺ 87 ሺ ሄክታር መሬት ላይ ጉዳት አድርሷል። ...

Read More »

በ2005 ዓም ኢትዮጵያ ከወደቁ አገራት ምድብ ተመደበች

ሰኔ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፎሬን ፖሊሲ መጽሄት በእያመቱ በሚያወጣው የወደቁ አገራት ሪፖርት ወይም በእንግሊዝኛው አጠራር ፌልድ ስቴትስ ኢንዴክስ ኢትዮጵያ እንደ አለፉት አመታት ሁሉ ዘንድሮው የወደቁ ወይም በመውደቅ ላይ ካሉ 20 አገራት መካከል አንዷ ሆና ተመድባለች። የህዝብ ቁጥር ፣ የስደተኛ ቁጥር፣ የህዝብ ብሶት፣ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ ያልተመጣጠነ እድገት፣ የመንግስት ህጋዊነት፣ ማህበራዊ አገልግሎት፣ የደህንነት ጥበቃ፣ የሊህቃን መከፋፈልና ...

Read More »

ፕሬዚዳንት ግርማ ለፍትሕ ሚኒስቴር ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

ሰኔ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከባድ የማታለል ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት፣ ዋና ጸሐፊና የአስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊ፣ የተከሰሱበት ክስ እንዲቋረጥላቸው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ፣ ለፍትሕ ሚኒስቴር የጻፉት ደብዳቤ ውድቅ መደረጉን  ሪፖርተር ዘገበ፡፡ ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ፤የአርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ ለፕሬዚዳንት ግርማ በጻፉላቸው የመማፀኛ ደብዳቤ መነሻነት ፤ፕሬዚዳንት ግርማ ...

Read More »

ምእመናን የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎችን ከሹመት አነሱ

ሰኔ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፊት ሶስት አመታት የመልካም አስተዳደር ችግር ፤የፍትህ እጦት እና ሙስና ተስተውሎባቸዋል ሲሉ ምእመናን ክስ የመሰረቱባቸው የባህርዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አመራሮች በህዝቡ እንዲነሱ ተደርጓል። ምእመኑ በአስተዳዳሪው ላይ ከፍትህ አካላት እስከ ሃገሪቱ ሊቀ ጳጳሳት ድረስ አቤቱታ ቢያሰሙም መፍትሄ በማጣታቸው የራሳቸውን እርምጃ ለመውሰድ መገደዳቸው ታውቋል። የፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዩርጊስ ገዳም ዋና ...

Read More »

አንዳንድ የፓርላማ አባላት አዲሱን የአማራ ህዝብ ቁጥር እንደማይቀበሉት አስታወቁ

ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ የሕዝብ ቆጠራ ኮምሽን በ1999/2000 ዓ.ም የሶስተኛው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት ይፋ በተደረገበት ወቅት በተለይ የአማራ ክልል ሕዝብ ብዛት ከሌሎች ክልሎች በተለየ ሁኔታ ከትንበያው ዝቅ ብሎ ተገኝቷል በሚል በቀድሞ የፓርላማ አባላት በቀረበው ቅሬታ ላይ ኮምሽኑ ፍተሻዎችን ቢያደርግም፣ አዲስ የቀረበውንም ሪፖርት አንዳንድ የፓርላማ  አባላት ሳይቀበሉት ቀርተዋል። የብአዴን ሊቀመንበር እና ...

Read More »

በመብራት ችግር ምክንያት ከባድ እንዱስትሪዎች ስራ እያቆሙ ነው

ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሃገሪቱ የሚገኙ ዋና ዋና የሲምንቶ ፋብሪቻዎች በመብራት ሃይል እጥረት ምክንያት ስራ ለማቆም ወይም ምርታቸውን ለመቀነስ መገደዳቸው ታውቋል። አቢሲኒያ ፣ ናሽናል፣ ሙገር እና ደርባን ሲምንቶ ፋብሪካዎች በመብራት ችግር ሳቢያ የምርት ሰአታቸውን ከመቀነስ ጀምሮ ለተወሰኑ ቀናት ስራ ማቆም ጀምረዋል። ሌሎች ፋብሪካዎች ደግሞ መብራት ቆጥበው እንዲጠቀሙ የሚያሳስብ ደብዳቤ ከመብራት ሀይል ደርሶአቸዋል። አንዳንድ ፋብሪካዎች ...

Read More »