መምህራን የነገው ጉባኤ ውጤት ለቀጣይ ትግሉ ወሳኝ ነው ይላሉ

የካቲት 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አለማቀፉ የመምህራን ማህበር ላቀረበው የደሞዝ ጭማሪ እስከ ጥር 30 ከመንግስት በኩል መልስ እንዲሰጠው ቢጠይቅም፣ እስካሁን ድረስ ምንም አይነት መልስ ሊሰጠው ባለመቻሉ በአማራ ክልል በጎንደር እና በጎጃም እንዲሁም በትግራይ የሚገኙ መምህራን የስራ ማቆም አድማ እስከ ማድረግ የደረሰ ተቃውሞ ማሰማታቸው ይታወሳል። አገራቀፉ የመምህራን ማህበር ይህን በተመለከተ ለነገ ሀሙስ የካቲት 15 ቀን 2004 ዓም አስቸኳይ ጉባኤ በራስ ...

Read More »

የፓኪስታን ኩባንያ ንብረት የሆነውን የሸንኮራ አገዳ ማሳ በእሳት ጋየ

የካቲት 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከመሬታቸውን በሀይል እንዲነሱ የተገደዱ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ አርሶአደሮች ተቃውሞዋቸውን ለመግለጥ፣ የፓኪስታን ኩባንያ ንብረት የሆነውን የሸንኮራ አገዳ ማሳ  በእሳት አጋዩ  ሪፖርተር እንደዘገበው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የስኳር ልማት ኮርፖሬሽንና የፓኪስታኑ ኩባንያ አል ሐበሻ ስኳር ሊያለሙ ያቀዱትን መቶ ሺሕ ሔክታር መሬት ከሰው ንክኪ ነፃ ለማድረግ እየተረባረቡ ነው። ይህ በጂማና በምሥራቅ ወለጋ ዞኖች መካከል ከበደሌ ከተማ ወደ ነቀምት ...

Read More »

መለስ ዜናዊን በመቃወም በለንደን ታላቅ ሰልፍ እንደሚካሄድ ታወቀ

የካቲት 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መለስ ዜናዊን የመሰለ አምባገነንና አሸባሪ ዘረኛ መሪ የሰላምና የመረጋጋት ዋስትና ሊሆን እንደማይችል ለአለም ህዝብ እናሳያለን! በሚል መሪ መፈክር ስር በተጠራዉ ታላቅ የተቃዉሞ ሰልፍ ላይ በለንደንና አካባቢዉ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዉያንና የሶማሊያ ተወላጆች እንደሚገኙ የሰልፉ አስተባባሪ ቡድን Net work against Repression & Injustice in Ethiopia ገልጿል። በሶማሊያ ጉዳይ የብሪታኒያ መንግሰት ሐሙስ የካቲት 23 ቀን 2012 በጠራዉ ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ የአቶ አንዱአለም አራጌ ደህንነት አደጋ ላይ ወድቋል አለ

የካቲት 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ዶ/ር ሀይሉ አርአያ፣ አቶ አስራት ጣሴ ፣ ኢ/ር ዘለቀ ረዲ እና አቶ ዳንኤል ተፈራ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኘው አቶ አንዱአለም አራጌ የካቲት 7 ቀን 2004 ዓም ከቀኑ 8 ሰአት ገደማ ለህይወቱ የሚያሰጋ ከባድ ድብደባ እንደተፈጸመበት ገልጠው፣ አቶ አንዱአለም በተፈጸመበት ድብደባ ምክንያት ከፍተኛ የአካልና የስነልቦና ጉዳት ...

Read More »

በጋምቤላ ከተገደሉት ሁለት ፖሊሶች መካከል አንዱ የአመራር አባል ነው

የካቲት 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ባለፈው ሳምንት ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላትና አንድ ሲቪል ሰራተኛ መገደላቸውን መዘገቡ ይታወሳል። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ባወጣው ዝርዝር ዘገባ ደግሞ የካቲት 8 ቀን ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ከተገደሉት መካከል አንደኛው የጋምቤላ ልዩ ሀይል አመራር መኮንን ሲሆን ፣ ከቆሰሉት ሲቪሎች መካከል ደግሞ  የሼክ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ የሆነው ሳዑዲ ስታር እርሻ ልማት ኩባንያ የፋይናንስ ኃላፊ ...

Read More »

በኩዌት ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ ኢትዮጵያዊ ወገንዋን አንቃ መግደሏን አመነች

የካቲት 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኩዌት ሃዋሊ በተባለዉ የመኖሪያ ህንፃ ላይ ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ ኢትዮጵያዊ ወገንዋን በገመድ አንቃ እንደገደለች ማመኗን አረብ ታይምስ የመረጃ ምንጭ ገልጧል “የቤት ሰራተኛ እራሷን በገመድ ሰቅላ አጥፍታለች “ በማለት ማንነቱ ካልታወቀ ሰዉ በደረሳቸዉ ጥሪ መሰረት የፀጥታ ሰራተኞችና አስቸኳይ የህክምና ቡድን /ፓራሜዲክስ/ በስፍራዉ ተገኝተዋል። ይሁን እንጂ የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራዎች በሚደረጉበት ወቅት ሟች እራሷን እንዳልገደለችና ለምን እንደሆነ ...

Read More »

በደቡብ የሶማሊያ ግዛቶች ጠንካራ ዉጊያዎች ተቀስቅሰዋል

የካቲት 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ሶማሊያ ቤይ እና ባኩል ክልሎች ዉስጥ በፌዴራል የሽግግሩ መንግሰትና በኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ጥምረት እንዲሁም በሌላ በኩል የአልቃይዳ አካል በሆነዉ አልሸባብ መካከል ጠንካራ ዉጊያ በመካሄድ ላይ እንዳለ ተገለፀ። በበርዳሌ ከተማ የሚገኙ የአይን ምስክሮች ለሸበሌ ሚዲያ በስልክ እንደገለፁት የአልሸባብ ተዋጊዎች ወታደራዊ ልምምድ በማድረግና ወደ ይዞታቸዉ እየገፉ በመምጣት ላይ ያሉትን የኢትዮጵያንና የሽግግር መንግሰቱን ወታደሮች ለመግታት መከላከያቸዉን ...

Read More »

በሆላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ እያዘጋጁ ነው

የካቲት 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኢምባሲ የቤኑሉክስ አባል አገራት በሆነት በቤልጂየምና በኔዘርላንድስ ከሚገኙ ኢትዮጵዮጵያውያን ጋር በዲያስፖራ ፖሊሲና  በአዲሱ የሊዝ አዋጅ ዙሪያ ለመወያየት የፊታችን ቅዳሜ ስብሰባ ጠርቷል። ኢሳት ከአዘጋጆቹ እንደተረዳው በስብሰባው እለት ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ድምጾችን ማሰማት ብቻ ሳይሆን፣ ይህን መንግስት በመቃወም የስደተኝነት ጥያቄ ጠይቀው የመኖሪያ ፈቃድ ያገኙትን ሰዎች በፊልም በተደገፈ ማስረጃ በማቅረብ፣ ለእየአገራቱ የስደተኝነት ጽህፈት ቤቶች ለማቅረብ ከፍተኛ ዝግጅት ...

Read More »

ከ40 በላይ መምህራን ይቅርታ ካልጠየቃችሁ ስራ አትጀምሩም ተብለው ታገዱ

የካቲት 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ተቃውሞ ያስነሱ ከ40 በላይ መምህራን ይቅርታ ካልጠየቃችሁ ስራ አትጀምሩም ተብለው ታገዱ፣ መምህራኑ ግን አሻፈረኝ ብለዋል በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ወረዳ ትምህረት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን ባለፈው ሳምንት የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ተከትሎ በተፈጠረ ውዝግብ ከ40 በላይ መምህራን ይቅርታ ካልጠየቃችሁ ስራ አትጀምሩም ተብለዋል። የወረዳው መስተዳድር ያቀረበውን የይቅርታ ጥያቄ አንቀበልም በማለት መምህራን በራሳቸው ጊዜ ማስተማር ቢጀምሩም፣ የወረዳው ...

Read More »

አቶ አንዱአለም አራጌ የመንፈስ መረጋጋት ይታይበታል ተባለ

የካቲት 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እሰከ ትናንት ድረስ ህክምና የተነፈገው የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ  የሆነው አንዱአለም አራጌ፣ ኢብሳ አስፋው በተባለ እስረኛ እንዲደበደብ ከተደረገ በሁዋላ፣ ትናንት እና ዛሬ በጥሩ የመንፈስ መረጋጋት ውስጥ ይገኝ እንደነበር ምንጮች ገልጠዋል። አሁንም እራሱን እንደሚያመው ይናገራል፣ ይሁን እንጅ የመንፈስ መረጋጋት ይታይበታል ያሉት አንድ ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን ይፋ የማናደርገው የቃሊቲ እስር ቤት ጠባቂ፣ ...

Read More »