Author Archives: mamoit

ፕሬዚዳንት ኦባማ በሶሪያ ላይ ለሚወስዱት ወታደራዊ ጥቃት ድጋፍ ለማሰባሰብ እየሞከሩ ነው

ነሃሴ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአገራቸውን ወሳኝ ፖለቲከኞች ድጋፍ ያገኙት ፕሬዚዳንት ኦባማ፣ አለማቀፍ ድጋፍ ለማግኘት የሚያደርጉትን ዘመቻ ዛሬ በስዊድን ጀምረዋል። አለም ያስቀመጠው ቀይ መስመር አለ፣ያም መስመር ” የኬሚካል የጦር መሳሪያዎችን መጠቀም አይቻልም” የሚል ነው፤ አለም ለዚህ ውሳኔው በጋራ ሊቆም ይገባል ብለዋል ፕሬዚዳንቱ። ከአውሮፓ አገራት መካከል  እስካሁን ድረስ ለአሜሪካ እርምጃ ድጋፏን የገለጸችው ፈረንሳይ ብቻ ናት። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሩሲያው ...

Read More »

በበባህርዳር አንድ የፖሊስ ኢንስፔክተር ተገደለ

ነሃሴ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወረዳ ሁለት እየተባለ ለሚጠራው አካባቢ ሀላፊ የነበረው ኢንስፔክተር ምትኩ ዛሬ ጠዋት በመኪና ተገጭቶ ሞቷል። ድርጊቱን የፈጸሙት ሰዎች እስካሁን ያልተያዙ ሲሆን ፣ ጉዳዩን በመመርመር ላይ የሚገኙት ዋና ኢንስፔተር ውበቱ ለኢሳት እንደገለጹት ድርጊቱ በምን ምክንያት እንደተፈጸመ ለማወቅ ምርመራ እየተካሄደ ነው ብለዋል። በግለሰቡ የተከፉ ሰዎች ሆን ብለው ገድለውት አምልጠዋል ይባላል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ኢንስፔክተሩ እስካሁን ያለን ...

Read More »

የአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ገጠመው፡፡

ነሃሴ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዩኒቨርስቲው የማስፋፊያ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ መንግሥት በተመደበ 859 ሚሊዮን 514 ሺ 332 ብር ከ42 ሳንቲም በ‹‹CDS consultancy›› ድርጅት አማካሪነት እና በሌሎች 15 ተቋራጮች ከ2001 ዓ/ም እስከ 2003 ዓ/ም ባሉት ጊዚያት  ተጀምሮ በመካሄድ ላይ ነው። አጠቃላይ ፕሮጀክቶቹን ለማጠናቀቅ የተያዘው የጊዜ ሠሌዳ ዝቅተኛው 2 ወር ከ15 ቀናት ከፍተኛው ደግሞ 49 ወራት ነው፡፡ በማስፋፊያ ፕሮጀክቱ እየተከናወኑ ከሚገኙ ...

Read More »

የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚ/ር በትላንትናው ዕለት በሒልተን ሆቴል ድንገት በጠራው የእራት ግብዣ አዲሱ ሚኒስትርን ከጋዜጠኞችና የኮምኒኬሽን ባለሙያዎች ጋር አስተዋወቀ፡፡

ነሃሴ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ አቶ በረከት ስምኦንን በመተካት በሚኒስትርነት ወደ ጽ/ቤቱ የመጡት አቶ ሬድዋን ሁሴንን ያስተዋወቁት አቶ ሽመልስ ከማል ሲሆኑ ሰውየው ከሚዲያ ጋር ባላቸው ቅርበት፣በአንደበተ ርዕቱነታቸው፣በፖለቲካ ዕውቀታቸው የላቁ መሆናቸውን ለጋዜጠኞች በመንገር አስተዋውቀዋቸዋል፡፡ ከሳምንት በፊት ከዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተርነት ተነስተው በመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት በሚኒስትር ዴኤታነት ማዕረግ የተሾሙት አቶ እውነቱ ደበላም በተመሳሳይ መንገድ ተዋውቀዋል፡፡ አቶ እውነቱ ወደ ...

Read More »

በአዳማ/ ናዝሬት የአንድነት ፓርቲ አባላት መዋከባቸው ታውቀ

ነሃሴ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በከተማዋ ለሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ የቅስቀሳ ወረቆቶችን ሲበትኑ የነበሩ ወጣቶች ለአጭር ጊዜ ተይዘው ተፈተዋል። ፓርቲው ሰለማዊ ሰልፍ እንዲአካሂደ ፈቃድ ከተሰጠው በሁዋላ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ እንጅ ወረቀት የመበተን ፈቃድ አልተሰጣችሁም በሚል ሰበብ ወጣቶቹ እንዲታሰሩ መደረጉ ታውቋል። ኢሳት ከኢህአዴግ የአዳማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ባገኘው አስተማማኝ መረጃ ፣ ፖሊሶችና የደህንነት ሀይሎች ፓርቲው የሚያደርገውን ...

Read More »

የመንግስት ሰራተኞች ምርጫ ካርድ መውሰድ አለመውሰዳቸውን እየተጠየቁ ነው

የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች በሚያዝያ ወር ለሚካሄደው የአካባቢና የአ/አ አስተዳደር ምርጫ ካርድ መውሰድና አለመውሰዳቸውን በቀጥታ እየተጠየቁ መሆኑን እንዲሁም አንዳንድ አባል ያልሆኑ ነዋሪዎች በካድሬዎችና በደህንነት ሰዎች የኢህአዴግ ዕጩ ሆነው በምርጫው እንዲቀርቡ ግፊት እየተደረገባቸው መሆኑን ምንጮች አመለከቱ፡፡ ለአንድ ወር ተካሄዶ ጥር 21 ቀን 2005 ዓ.ም የመራጮች መደበኛ ምዝገባ ቢጠናቀቅም በተለይ በአዲስ አበባ ...

Read More »

ኢሳት በስዊድንና በኖርዌይ የተሳካ ዝግጅት አደረገ

የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቅዳሜ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ፌብርዋሪ 9፣ 2013 ከሰዓት በኋላ ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በተካሄድው የኢሳት የገንዘብ ማሰባሰባቢያ ዝግጅት ላይ ከጨረታ ከመቶ ሰላሳ ሺህ የስዊድን ክሮነር ወይም ከሃያ ሺህ በላይ የአሜሪካን ዶላር ተሰበሰበ። ይህንን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ የተገኘው በዝግጅቱ ላይ የታላቁ ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ፓትሪያክ እና የጸረ ፋሽስት ታጋይ ...

Read More »

እውቁና አንጋፋው ድምፃዊ፤ አርቲስ ታምራት ሞላ አረፈ

የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ እንደ ቅርስ ከሚታወቁት አንጋፋ ድምፃውያን አንዱ የሆነው አርቲስት ታምራት ሞላ አረፈ። ታምራት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ከ 50 ዓመታት በላይ ያገለገለ ስመ-ጥር አርቲስት ነው። ከዓመታት በፊት በሉኪሚያ (የደም ካንሰር) የተጠቃው ተወዳጁ የባህል ቅርስ፤ከህመሙ ጋር ግብ ግብ ሲያደርግ ከቆዬ በሁዋላ ትናንት ሌሊት በአዲስ አበባ ህይወቱ አልፏል። በጎንደር ከተማ የተወለደው እና ገና በወጣትነት በሠራዊቱ ...

Read More »

የጸጥታ ሹሙ የኦሮሚያን መሬት ለሶማሊ ክልል አሳልፈን አንሰጥም አሉ

የካቲት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት 4 ቀናት በተካሄደው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ከፍተኛ   አጀንዳ ሆኖ የቀረበው በክልሉና በሶማሊ ክልል መካከል ያለው የብሄር ግጭት ነው። ከህመማቸው በመጠኑም ቢሆን አገግመው በስብሰባውላይ የተገኙት የክልሉ ፕሬዚዳንት፣ አቶ አለማየሁ አቶምሳ እና የክልሉ የጸጥታ ሹም ፍቃዱ ሰቦቃ ከምክር ቤት አባላት ለተነሳው ጥያቄ መልስ ለመስጠተ ሞክረዋል። ከምስራቅ ኦሮሚያ እና ከቦረና ዞን የመጡ የምክር ቤት ...

Read More »

በትላንት አርብ የጁማ ጸሎት ተሳትፈዋል የተባሉ ሙስሊሞች ታሰሩ

የካቲት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢ ከአዲስ አበባ የላከው ሪፖርት እንዳመለከተው ከፍተኛ ቁጥር ባስተናገደው የትናንት የጁማ ተቃውሞ በአስተባባሪነት የተጠረጠሩ ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ እየተለቀሙ በመታሰር ላይ ናቸው። በመርካቶ፣ ፒያሳ ፣ ጉለሌ፣ ሰባተኛ እና በሌሎችም አካባቢዎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሙስሊሞች ተይዘው ታስረዋል። ከታሰሩት መካከል አብዛኞቹ ወጣቶች ሲሆኑ፣ አንዳንዶች ወደ ማእከላዊ እስር ቤት ሌሎች ደግሞ በየአካባቢያቸው ባሉ ፖሊስ ጣቢያዎች ተወስደዋል። ...

Read More »