Author Archives: ESAT Amsterdam

በበሁሌ ሆራ በመከላከያና ኦነግ መካከል የተኩስ ለውውጥ ተካሂዷል የተባለው ስህተት ነው ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጹ

በበሁሌ ሆራ በመከላከያና ኦነግ መካከል የተኩስ ለውውጥ ተካሂዷል የተባለው ስህተት ነው ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጹ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 20 ቀን 2011 ዓ/ም ) ነዋሪዎች እንደገለጹት ባለፈው አርብ ጥቅምት 16 ቀን 2011 ዓም ወጣቶች ከቡሌ ሆራ ወደ ሞያሌ፣ ከቡሌሆራ ወደ አዲስ አበባና ወደ ሻኪሶ የሚወስዱ መንገዶችን የዘጉ ሲሆን፣ የመከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው በመሄድ የሞያሌን መንገድ አስከፍተዋል። መንገድ አስከፍተው ሲመለሱ የነበሩ ...

Read More »

በሃረር ለረጅም ጊዜ ሲያገለግል የነበረው ቄራ ተዘጋ

በሃረር ለረጅም ጊዜ ሲያገለግል የነበረው ቄራ ተዘጋ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 20 ቀን 2011 ዓ/ም ) በከተማው ቀበሌ 8 የሚገኘው ቄራ በመዘጋቱ እርድ መቆሙን የከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል። አንዳንድ ነዋሪዎች ቄሮዎች እንዳዘጉት የገለጹ ሲሆን፣ የቀበሌ 8 የቄሮ ተወካይ ወጣት ሚስባህ ግን ቄሮ ቄራው እንዲዘጋ አለመስደረጉንና የወረዳው መዘጋጃ ከጤና ጋር በተያያዘ መዝጋቱን ገልጿል። የሸንኮር ወረዳ አስተዳደሪ አቶ አብዱረህማን አሰፋም እንዲሁ ቄራው የተዘጋው ...

Read More »

በምዕራብ ወለጋ እንዲሁም በምስራቅ ጉጂ የኦነግ ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት እርምጃ በመወሰድ ላይ ነው።

በምዕራብ ወለጋ እንዲሁም በምስራቅ ጉጂ የኦነግ ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት እርምጃ በመወሰድ ላይ ነው። ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 19 ቀን 2011 ዓ/ም ) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ካለፈው አርብ ጀምሮ በኦነግ ስም በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ላይ የመንግስት ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ በብዙ ታጣቂዎች ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ ደርሷል። የኦነግ ወታደሮችን ትጥቅ መፍታት የተቃወሙ ወጣቶች በየአካባቢው የተቃውሞ ሰልፎችን ሲያደርጉ ሰንብተዋል። በምዕራብ ወለጋ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ...

Read More »

ከአማሮ ወረዳ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ጉማይዴ ገቡ

ከአማሮ ወረዳ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ጉማይዴ ገቡ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 19 ቀን 2011 ዓ/ም ) ከአማሮ ወረዳ ቡኒቲ ቀበሌ የተፈናቀሉ በርካታ የአማራ ተወላጆች በሰገን ዞን ዋና ከተማ ጉማይዴ ላይ መስፈራቸውን ወኪላችን ገልጿል። ነዋሪዎች እንደሚሉት በጉማይዴ ከተማ ጳጉሜ 2 ቀን 2010 ዓም በነበረው ሰልፍ ላይ የአማራ ተወላጆች ሰልፍ ሲወጡ የኮይሬ ተወላጆች ሰልፍ ባለመውጣታቸው የተጀመረው ጸብ፣ ጥቅምት 16 ቀን 2011 ዓም ...

Read More »

በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ተደረጉ

በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ተደረጉ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 19 ቀን 2011 ዓ/ም ) የራያ እና ወልቃይት የማንነት ጥያቄ እንዲከበር፣ በጣና ሐይቅንና የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስያናትን እንታደግ በሚል መሪ ቃል በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ትዕይንተ ህዝብ ተደረገ። ካለ ህዝብ ውሳኔ ወደ ትግራይ ክልል የተካለሉት ወልቃይቶችና ራያዎች ማንነታቸው እንዲከበር፣ ሰብዓዊ መብታቸውን የሚጥሱ የትግራይ ክልል ልዩ ጦር አባላት አካባቢውን ለቀው ...

Read More »

በነጭ ሳር ፓርክ ታጣቂዎች ተጣቂዎች ቢያንስ 4 ሰዎችን ገደሉ

በነጭ ሳር ፓርክ ታጣቂዎች ተጣቂዎች ቢያንስ 4 ሰዎችን ገደሉ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 16 ቀን 2011 ዓ/ም ) በአርባምንጭ ከተማ ዙሪያ በሚገኘው የነጭ ሳር ፓርክ ውስጥ የመሸጉ ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ 4 ሰዎች ሲገደሉ 3 ሰዎች ደግሞ ክፉኛ መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ጥቃቱን የኦነግ ታጣቂዎች እንዳደረሱት ይናገራሉ ኢሳት የአካባቢውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረገው ...

Read More »

በዱራሜ ስራ እንዲሰጣቸው በሰላማዊ ሰልፍ የጠየቁ የዩኒቨርስቲ ምሩቃን በፖሊሶች ተደበደቡ

በዱራሜ ስራ እንዲሰጣቸው በሰላማዊ ሰልፍ የጠየቁ የዩኒቨርስቲ ምሩቃን በፖሊሶች ተደበደቡ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 16 ቀን 2011 ዓ/ም ) በከምባታ ጠምባሮ ዞን ካለፉት 4 ዓመታት ወዲህ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ተመርቀው ስራ ያጡ ወጣቶች ወደ ዞን መስተዳደር ምክር ቤት ማምራታቸውን ተከትሎ በፖሊሶች ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። ተማሪዎቹ ቀደም ብለው ጥያቄያቸውን ለመስተዳድሩ አቅርበው ለዛሬ አርብ ተቀጥረው የነበረ ቢሆንም፣ በቀጠሮአቸው መሰረት ወደ መስተዳድሩ ሲሄዱ ያጋጣማቸው የፖሊስ ...

Read More »

በታንዛኒያ ውቂያኖስ ዳርቻ በጀልባ ሲጓዙ የነበሩ ሰባት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ተገልብጠው ህይወታቸውን አጡ።

በታንዛኒያ ውቂያኖስ ዳርቻ በጀልባ ሲጓዙ የነበሩ ሰባት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ተገልብጠው ህይወታቸውን አጡ። ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 16 ቀን 2011 ዓ/ም ) መነሻቸውን ከኬኒያ በማድረግ ወደ ደቡብ አፍሪካ በመጓዝ ላይ ከነበሩት 13 ተጓዦች ውስጥ ባጋጠማቸው የጀልባ መገልበጥ አደጋ ሰባቱ መሞታቸውን ማክሰኞ ዕለት የታንዛኒያ ፖሊስ አስታውቋል። ጀልባዋ ሰኞ ማለዳ ላይ ህንድ ውቅያኖስ የኬኒያ እና የታንዛኒያ የባህር ዳርቻ በጀልባ ጉዞዋቸውን በማድረግ ላይ እያሉ ...

Read More »

የሰገን ዞንን እንደገና ለማዋቀር የተወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ ነዋሪዎች ነቀፋም ድጋፍም እየገለጹ ነው

የሰገን ዞንን እንደገና ለማዋቀር የተወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ ነዋሪዎች ነቀፋም ድጋፍም እየገለጹ ነው ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 15 ቀን 2011 ዓ/ም ) የሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን በ2003 ዓ/ም ኮንሶ፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ ሰገን ከተማ/ጉማይዴ/፣ ቡርጂ እና አሌን በማጣመር ከተመሰረተ በሁዋላ አልፎ አልፎ የተቃውሞና የግጭት ማዕከል ሆኖ ቆይቷል። በተለይ የኮንሶ ህዝብ በዚህ ዞን ስር ለመቀጠል ፈቃደኛ ባለመሆኑ፤ የተለያዩ ተከታታይ ተቃውሞዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል። ከ2008 ...

Read More »

የትግራይ ክልል የአማራ ክልል ይቅርታ እንዲጠይቅ አሳሰበ

የትግራይ ክልል የአማራ ክልል ይቅርታ እንዲጠይቅ አሳሰበ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 14 ቀን 2011 ዓ/ም ) የትግራይ ክልል መንግስት፣ የአማራ ክልል መንግስት ጥቅምት 13 ቀን 2011 ዓም በወልቃይትና በራያ የማንነት ጥያቄዎች ዙሪያ ያወጣውን መግለጫ የሚቃወም መግለጫ ያወጣ ሲሆን፣ በመግለጫውም “የትግራይ ክልል ከመግለጫው በተቃራኒ የሁሉም ብሄር ብሄረሰብ ተወላጆች ሕገ መንግስታዊ መብታቸውና ነፃነታቸው ተከብሮ በሰላምና በክብር የሚኖሩባት ክልል ሆና እያለች ዜጎች በማንነታቸው ...

Read More »