Author Archives: Eyerusalem Eshete

ሼህ ወርቁ ኑሩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 2/2011)በደቡብ አፍሪካ ለኢትዮጵያ ነጻነትና ፍትህ ድምጻቸውን በማሰማት የሚታወቁት ሼህ ወርቁ ኑሩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ሼህ ኑሩ ላለፉት 20 ዓመታት በደቡብ አፍሪካ በሚካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎችና ህዝባዊ ስብሰባዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ትግል አንስቶ በዋና ዋና የፖለቲካ ንቅናቄዎች ውስጥ ሚናቸው በጉልህ የሚጠቀሰው ሼህ ኑሩ በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ የነጻነት አርማ ተደርገው እንደሚታዩም ...

Read More »

የቤንሻንጉል ተፈናቃይ እናቶች በመጠለያ ውስጥ ልጆቻቸውን ተገላገሉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 2/2011) ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ተፈናቅለው በኦሮሚያ ክልል ከተጠለሉ ተፈናቃዮች ውስጥ ከ20 በላይ ነፍሰ ጡር እናቶች በመጠለያ ውስጥ መገላገላቸው ታወቀ። ሌሎች 53 ወራቸው የገባ ነፍሰ ጡሮች የመውለጃ ጊዜያቸውን እየጠበቁ መሆናቸው ተመልክቷል። የነቀምቴ ሪፈራል ሆስፒታል ነፍሰ ጡሮችንና እመጫቶቹን በመንከባከብ ላይ መሆኑን መረጃው አመልክቷል። የቤንሻንጉል ክልል ካማሼ ዞን ባለስልጣናት ከስብሰባ ሲመለሱ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በታጣቂዎች መገደላቸውን ተከትሎ በካማሼ ዞን ሰላማዊ ነዋሪዎች ...

Read More »

በሸካ ዞን ስደስት ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 2/2011) በሸካ ዞን ቴፒ በየኪ ወረዳ  እርምጭ ቀበሌ  ጎረፌ በሚባል  መንደር  በተፈጸመ ጥቃት ስደስት ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በጥቃቱ ምክንያት ከሰባ በላይ አባዎራዎች ተፈናቅለው በቴፒ ከተማ ሁለገብ አዳራሽ መጠለላቸው ተነግሯል። በሸካ አሁንም አካባቢውን ለቃችሁ ሒዱ በሚል ጥቃቱ ተጠናክሮ በመቀጠሉ መንግስት ድርጊቱን እንዲያስቆም የአካባቢው ነዋሪዎች ጥሪ አቅርበዋል። በሸካ ዞን እርምጭ ቀበሌ  አካባቢ  በሚኖሩ  በተወሰኑ ብሄረሰብ  አባላት ...

Read More »

የኢትዮጵያ አየር ሃይል አውሮፕላን የምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 1/2011)ከድሬደዋ ወደ ቢሾፍቱ ከአንድ ወር በፊት ሲበር የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር ሃይል አውሮፕላን የምርመራ ውጤት ይፋ ተደረገ። የኢትዮጵያ አየር ሃይል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት አውሮፕላን ምንም የቴክኒክ ችግር እንዳልገጠመው በምርመራ ተረጋግጧል። ነሐሴ 24/2010 ከረፋዱ 3 ሰአት ከ40 ደቂቃ ከድሬደዋ መነሳቱ የተገለጸው የበረራ ቁጥር 808 ዳሽ 6 አውሮፕላን፣ኤጀሬ በተባለ ከተማ አቅራቢያ መከስከሱ ይታወሳል። አብራሪዎቹንና የቴክኒክ ባለሙያዎቹን ...

Read More »

ኦነግ ትጥቅ አልፈታም ማለቱ ተገቢ አይደለም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 1/2011)የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ሊቀመነበር አቶ ሌንጮ ለታ ኦነግ ትጥቅ አልፈታም ማለቱ ተገቢ አይደለም አሉ። ወጣቱ በባዶ እጁ ታንክ ፊት በሚጋፈጥበት ጊዜ የኦነግ ሰራዊት የት ነበር ሲሉ አቶ ሌንጮ ለታ በሀገር ውስጥ ከሚሰራጨው አሀዱ ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ገልጸዋል። ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት ከፈለግን በሀገር ውስጥ መኖር ያለበት ሰራዊት የመንግስት ብቻ መሆን አለበት ያሉት አቶ ሌንጮ ለታ የኦነጉ ሊቀመንበር አቶ ...

Read More »

መንግስት ከፍተኛ ሹም ሽር ሊያደርግ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 1/2011) መንግስት በቀጣይ ሳምንት ከፍተኛ ሹም ሽር እንደሚያደርግ ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር የሚወስነው ረቂቅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ለፓርላማ መላኩም ይፋ ሆኗል። በሚቀጥለው ሳምንት በፓርላማ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ሕግ የሚኒስትር መስሪያ ቤቶችን ቁጥር ከ28 ወደ 20 ዝቅ እንደሚያደርገው ተመልክቷል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትላንት የጸደቀውና በሚቀጥለው ሳምንት ፓርላማ ጸድቆ ስራ ላይ እንደሚውል በሚጠበቀው የአስፈጻሚ አካላትን ...

Read More »

መንግስት ኦነግን ትጥቅ ያስፈታል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 30/2011) መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ሲል ኦነግን ትጥቅ ለማስፈታት እንደሚገደድ የኢትዮጵያ መንግስት አስታወቀ። የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ድኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ መንግስት የታጠቁ ሃይሎች በሃገር ውስጥ እንዲንቀሳቀስ በማድረግ ሁለት መንግስት እንዲኖር አይፈቅድም ብለዋል። ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለማድረግ የወሰነ ሃይል በመሳሪያ ጭምር እንደማይንቀሳቀስ የገለጹት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ኦነግ ትጥቅ ለመፍታት አልተስማማንም የሚለውን አቋሙን ...

Read More »

በሃዋሳ አሮጌው ገበያ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በእሳት ወደመ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 30/2011) በአዋሳ ከተማ የሚገኘው አሮጌው ገበያ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ወደመ። በገበያው የተነሳውን እሳት ለማጥፋት የከተማው ማዘጋጃ ቤት የእሳት አደጋ ሰራተኞች በስፍራው የደረሱት እሳቱ ከተነሳ ከ1 ሰአት ተኩል በኋላ መሆኑም ታውቋል። ከአዋሳ ከተማ መቆርቆር ጋር አብሮ እንደተመሰረት የሚነግርለት ገበያ በከተማው አዲስ የገበያ ስፍራ በመመስረቱ አሮጌው ገበያ በመባል ይጠራል። በዚህ ስፍራ ለረጅም ዘመናት በንግድ ስራ የተሰማሩ የከተማው ነዋሪዎች ሀብት ...

Read More »

የአዲስ አበባ ወጣቶች ከጦላይ ማሰልጠኛ ሊወጡ ነው።

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 30/2011)ከአዲስ አበባ ከተማ የታፈሱትና ወደ ጦላይና ሌሎች ማሰልጠኛዎች የተወሰዱት ወጣቶች ስልጠናቸውን ጨርሰው በቅርቡ እንደሚወጡ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ወጣቶቹ የተያዙት ፖሊስ ላይ ድንጋይ ሲወረውሩና ችግር ሲፈጥሩ የነበሩ ናቸው ብለዋል። አንድም የታሰረ ወጣት የለም ያሉት ኮሚሽነሩ ወጣቶቹ የተያዙት እንዲታሰሩ ሳይሆን ከህገወጥ ተግባር እንዲወጡና ስለህግ የበላይነት ስልጠና እዲያገኙ ነው ...

Read More »

የመከላከያ ሰራዊት አባላት የደሞዝ ጭማሪና የጥቅማጥቅም ጥያቄ አነሱ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 30/2011) በአዲስ አበባ ወደ ቤተ መንግስት በማምራት የደሞዝ ጭማሪና ጥቅማጥቅም ያነሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጋር መወያየታቸውን የፌዴራል ፖሊስ ጄኔራል ኮሚሽነር አቶ ዘይኑ ጀማል ገለጹ። ወታደሮቹ ከሃዋሳ መጥተው ለጸጥታ ጥበቃ በቡራዩ ተልእኮ ላይ የነበሩ የሰራዊት አባላት መሆናቸውንም ኮሚሽነሩ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልጸዋል። በቁጥር 250 የሚደርሱት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከነጠበንጃቸው ወደ ቤተመንግስት በማምራት ጠቅላይ ...

Read More »