Author Archives: Eyerusalem Eshete

በኦሮሚያና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ግጭት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተሳታፊ መሆናቸው ታወቀ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 18/2010)በኦሮሚያና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እንደገና ባገረሸው ግጭት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተሳታፊ መሆናቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ንጹሃን ሰላማዊ ሰዎችን ሲገድሉ በነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይም ርምጃ መወሰዱ ታውቋል። በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ እንደገና ግጭት ማገርሸቱን መንግስት በሳምንቱ መጨረሻ ማረጋገጫ ሰጥቷል። በኦሮሚያና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አዲስ ባገረሸው ግጭት ባለፈው ሳምንት ብቻ 20 ሰዎች መገደላቸውን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ቃል ...

Read More »

ወይዘሮ አዜብ መስፍን ከህወሃት ስራ አስፈጻሚ አባልነት ታገዱ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 18/2010)ከሁለት ወራት በላይ የዘለቀው የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤትን ወይዘሮ አዜብ መስፍንን አገደ። ማዕከላዊ ኮሚቴው የፓርቲውን ሊቀመንበርና ሌላ አንድ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዝቅ ማድረጉን የትግራይ ክልል ቴሌቪዥን አስታውቋል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን ተከትሎ የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሊቀመንበርነትን ላለፉት አምስት አመታት የያዙት አቶ ...

Read More »

በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች ድንበር አካባቢ ዳግም ግጭት ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 15/2010)ጋብ ብሎ የነበረው በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች ድንበር አካባቢ ዳግም ግጭት ተቀሰቀሰ። በሞያሌ አቅራቢያ ቦርቦር በተባለው አካባቢ በተቀሰቀሰው በዚሁ ግጭት ከሁለቱ ወገኖች 27 ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። የህወሃት ልዩ ኮማንዶ በአካባቢው ከገባ በኋላ ግጭቱ እንደተቀሰቀሰ የጠቀሱት የኢሳት ምንጮች በግድያው ላይ የኮማንዶ ሃይሉ በቀጥታ መሳተፉንም ገልጸዋል። በሌላ በኩል በአርሲ ነገሌ የመንግስት ካድሬዎች አቀናብረውታል በተባለ ጥቃት በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የኢሳት ምንጮች ...

Read More »

በግብጽ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት ቢያንስ 235 ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 15/2010)በግብጽ ሳይናይ ግዛት በአንድ መስጊድ ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት ቢያንስ 235 ሰዎች ሲገደሉ 130 ሰዎች ቆስለዋል። የሟቾቹም ሆነ በጥቃቱ የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል መረጃዎች ጠቁመዋል። የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የሶስት ቀናት ብሔራዊ የሀዘን ቀንም አውጀዋል። እስካሁንም ለጥቃቱ በይፋ ሃላፊነት የወሰደ አካል የለም ። በግብጽ ሳይናይ ግዛት ዛሬ በአንድ መስጊድ ላይ በደረሰው የሽብር ጥቃት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰአት ...

Read More »

አዲሱ የዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት ቃለ መሃላ ፈጸሙ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 15/2010)ሮበርት ሙጋቤን የተኩት አዲሱ የዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት ኤምርሰን ናንጋግዋ ቃለ መሃላ ፈጸሙ። ቀደም ሲል በሮበርት ሙጋቤ ከምክትል ፕሬዝዳንትነት የተባረሩት ኤመርሰን ናንጋግዋ በሕዝብ ግፊት ሕገ መንግስቱን መሰረት በማድረግ የሀገሪቱ መሪ ሆነዋል። ፕሬዝዳንቱ ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በኋላ በዚምባቡዌ ዲሞክራሲያዊ ስረአት እንደሚያሰፍኑና በሀገሪቱ አድልዎ የሌለበት የሁሉም ዜጎች ርዕሰ ብሔር እንደሚሆኑ ቃል መግባታቸውን ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል።

Read More »

የሀዋሳ መምህራን የስራ ማቆም አድማ መቱ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 15/2010)የሀዋሳ ታቦር ሁለተኛ ደረጃ መምህራን ለአንድ ቀን የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ተገለጸ። መምህራንን የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ለማድረግ በደቡብ ክልል መንግስት የወጣው መመሪያ ተፈጻሚ ሳይሆን ቤት እንዳገኘን ተደርጎ ሪፖርት መቅረቡና በመገናኛ ብዙሃን መነገሩ አስቆጥቶናል ያሉት መምህራን የአንድ ቀን ስራ በማቆም ወደክልሉ መስተዳድር በመሄድ ቅሬታቸውን ማቅረባቸው ተገልጿል። በከተማዋ የሚገኙ ሌሎች ትምህርት ቤት መምህራንም እንዲቀላለቀሉ ተጠይቋል። በሌላ በኩልም በዙር ሀዋሳ ለደረሰው ...

Read More »

የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከዱ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 15/2010)ከሞያሌ በሳምንቱ መጀመሪያ የተሰወሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መክዳታቸውን ምንጮች ለኢሳት አረጋገጡ። የከዱት የሰራዊቱ አባላት ቁጥርም 38 እንደሆነ ምንጮቹ ገልጸዋል። እነሱን ለመፈለግ የወጣው ሃይልም አለመመለሱ ታውቋል። ሆኖም ለአሰሳ በወጣው ሃይል ውስጥ በተፈጠረ ውዝግብ አንድ ወታደር ሲገደል አንድ መቁሰሉን ምንጮቹ ተናግረዋል። ጥቃቱ የተፈጸመባቸው የኦሮሞ ተወላጅ ወታደሮች መሆናቸውም ተመልክቷል። በሳምንቱ መጀመሪያ ከሞያሌ ተነስተው ለአሰሳ የወጡት ወታደሮች ከ24 ሰአታት በላይ መሰወራቸውን ተከትሎ ...

Read More »

የኦሮሚያ ክልል የሜቴክን ህገወጥ ድርጊት ማስቆሙን አስታወቀ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 15/2010) የኦሮሚያ ክልል ውሃ ሃብት ቢሮ ሜቴክ ከክልሉ የድንጋይ ከሰል በማውጣትና በመሸጥ ሲያከናውን የነበረውን ህገወጥ ድርጊት ማስቆሙን አስታወቀ። ቢሮው “ህገ ወጥ የሆነ የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባር በድብቅ ቢፈጸምም ከብዙሃኑ ህዝብ እይታ ግን ፈጽሞ ሊሰወር አይችልም” በሚል ባወጣው መግለጫ ሜቴክን ብቻ ሳይሆን የክልሉን ሃብት በመዝረፍ የተሰማሩ አካላት ላይ የምወስደውን ርምጃ እቀጥላለሁ ብሏል። የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን /ሜቴክ/በሕግ ከተቋቋመበትና ከተሰጠው ...

Read More »

በመከላከያ አመራር ላይ ከፍተኛ ብወዛ እየተደረገ ነው

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 15/2010) በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት ተከትሎ በመከላከያ አመራር ላይ ከፍተኛ ብወዛ እየተደረገ መሆኑ ተሰማ። ብወዛው በተለይ የኦሮሞና አማራ ተወላጆች ላይ የተነጣጠረ መሆኑንም ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። በጄኔራል መኮንኖች አካባቢ አመራሩ በሕወሃት ጄኔራሎች በመያዙ ብወዛው ከዚያ በመለስ ባለው የስልጣን መዋቅር ላይ ማተኮሩ ተመልክቷል። በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ በተጠናከረው ብወዛ በቅድሚያ የተሸጋሸጉ የ12 መኮንኖች ዝርዝር ለኢሳት ደርሶታል። በዚህም መሰረት ኮለኔል አበራ ለማ፣ኮለኔል ...

Read More »

አመታዊው የምስጋና ቀን ተከብረ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 14/2010)አመታዊው የምስጋና ቀን/ታንክስ ጊቪንግ/ዛሬ በአሜሪካኖች ዘንድ ተከብሮ ዋለ። በአሜሪካ የሚኖሩ አንዳንድ ኢትዮጵያውያንም ሁኔታና አቅም በፈቀደ መጠን በአሉን ያከብራሉ። በአሜሪካውያኑ ዘንድ በያመቱ በህዳር ወር 4ኛው ሀሙስ ላይ የሚከበረው የምስጋና ቀን/Thanksgiving/ ምስጋና የሚሰጥበትና ቤተሰብና ጓደኛ ሰብሰብ ብሎ የሚያከብረው ቀን ነው። በአሜሪካና ካናዳ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም ሁኔታው እንደፈቀደላቸው ሰብሰብ ብለው ያከብሩታል። በአሉ በካናዳ ባለፈው ወር ተከብሯል። በአሉ በካሪቢያን ደሴቶችና በአፍሪካም በላይቤሪያ እንደሚከበር ...

Read More »