Author Archives: Eyerusalem Eshete

ህወሃት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላቱን ቁጥር ከ11 ወደ 9 ዝቅ አደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 9/2011) የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ የድርጅቱን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ቁጥር ከ11 ወደ 9 ዝቅ እንዲል ማድረጉን አስታወቀ። ማዕከላዊ ኮሚቴው ቁጥሩን ዝቅ እንዲል ያደረገው ከዚህ በፊት ያልደርጅቱ ጉባኤ ፈቃድ ቁጥሩን ከፍ በማደረጉ ነው ተብሏል። በዚሁ መሰረት በቅርቡ የስራ አስፈጻሚ አባል የነበሩት አቶ በየነ መክሩ እና ዶክተር አክሊሉ ሃይለሚካኤል እንዲቀነሱ ተደረገዋል። ሕወሃት የስራ አስፈጻሚውን ቁጥር ሕገ ደንቡን በመጣስ ከዘጠኝ ወደ ...

Read More »

አብዲ ኢሌ ከእስር ቤት ሊያመልጡ ነበር ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 19/2011) የሶማሌ ክልል የቀድሞ ፕሬዝዳንት ከእስር ቤት ሊያመልጡ ሙከራ ማድረጋቸውን  ፓሊስ ለፍርድ ቤት ተናገረ። ፓሊስ በአቶ አብዲ ኢሌ ላይ ባደረገው ምርመራም በሶማሌ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ ተጠያቂ መሆናቸውን ማመናቸውንና ለዚህም ይቅርታ መጠየቃቸውን ለፍርድ ቤቱ አስታውቋል። የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ ኢሌ መሃመድ ክልሉን በሚያስተዳድሩበት ወቅት ክልሉን እንደፈለጋቸው ሲያሽከረክሩና ተቆጣጣሪ የሌላቸው በሚመስል መልኩ ዜጎችን በመግደል፣በማሰርና ክልሉን ለቀው እንዲሰደዱ በማድረግ ...

Read More »

አቶ ታዬ ደንደአ ወደ ኦዴፓ ጽሕፈት ቤት ተዛወሩ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 9/2011) የፌደራል ጠቅላይ አቃቤህግ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ታዬ ደንደአ ወደ ኦዴፓ ጽሕፈት ቤት ተዛወሩ። ለሶስት ወራት ከቆዩበት የፌደራል የሃላፊነት ቦታ ተነስተው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኦዴፓ ማዕከላዊ ጽሕፈት ቤት  የሕዝብ ግንኙነት ክፍል በምክትል ሃላፊነት እንዲሰሩ መውሰኑን ለማወቅ ተችሏል። አቶ ታዬ ደንደአ ከፌደራል መስሪያ ቤት ወደ ክልላዊ ፓርቲ ጽሕፈት ቤት እንዲዛወሩ የተደረገበት ምክንያት ባይታወቅም በአዲሱ የኦዴፓ መዋቅራዊ አደረጃጀት ...

Read More »

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪ አቀረበ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 19/2011) አቶ ሔኖክ አክሊሉና ሚካኤል መላከ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪ አቀረበ። የአዲስ አበባ ከተማ እንደሌሎች ክልሎች ሁሉ ሙሉ መብት እንዲሰጣት በመንቀሳቀሳቸው መታሰራቸውን የገለጸው አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከፍልስጤም ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ስልጠና ወስደዋል የሚል ክስም እንደቀረበባቸው አመልክቷል። ከትላንት በስቲያ አዲስ አበባ ላይ ተይዘው ትላንት ፍርድ ቤት የቀረቡት ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉና አቶ ሚካኤል መላከ በአስቸኳይና ...

Read More »

የአዲስ አበባ ወጣቶች ከጦላይ ወታደራዊ ካምፕ ተለቀቁ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 8/2011) ባለፈው ወር መጀመሪያ በጅምላ ታፍሰው ወደ ጦላይ ወታደራዊ ካምፕ ተወስደው የነበሩ ከ1ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ወጣቶች ዛሬ መለቀቃቸው ተገለጸ። ለወጣቶቹ ስልጠና ተሰጥቶ መለቀቃቸውን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወደ ቤተሰቦቻቸው የማጓጓዝ ስራ መጀመሩን አስታውቋል። ከፍተኛ ተቃውሞ ያስነሳውና ህገመንግስታዊ መብቶችን የጣሰ ነው የተባለው የአዲስ አበባ ወጣቶች እስርን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ያለአግባብ የታሰሩ ከነበሩም ለለውጡ የከፈሉት መስዋዕትነት ...

Read More »

ሁለት የሰብዓዊ መብትና የህግ ባለሙያዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 8/2011)የአዲስ አበባ ወጣቶችን በማደራጀት ክስ የተመሰረተባቸው ሁለት የሰብዓዊ መብትና የህግ ባለሙያዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ። ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉና ሚካዔል መላከ አዲስ አበባ ከሌላ አካባቢ በመጣ ሰው አትተዳደርም የሚል ቅስቀሳ በማድረግና የአዲስ አበባ ወጣቶችን ሲያደራጁ ነበር የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። የፖሊስ ክስ ላይ ለዚህ እንቅስቃሴ የሚረዳ ግንኙነት ከፍልስጤም ኤምባሲ ጋር መደረጉን የሚያመለክት ነው። የአዲስ አበባ ወጣቶችን ለማደራጀት ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ ሌሎች ...

Read More »

የስደተኞች ቁጥር ወደ አንድ ሚሊየን ተጠጋ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 8/2011) በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞች ቁጥር ወደ አንድ ሚሊየን መጠጋቱን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አስታወቀ። ከጥር እስከ ነሐሴ ብቻ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ስደተኞች ቁጥር ከ36 ሺ በላይ መሆኑን የገለጸው ይህው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካል የኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር መከፈቱን ተከትሎም የስደተኞቹ ቁጥር መጨመሩን አመልክቷል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር እስከ ነሐሴ 31/2018 በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞች ቁጥር 905ሺ 831 መድረሱን የገለጸው የተባበሩት ...

Read More »

ለውጡን ለማደናቀፍ የታጠቁ ወታደሮች ወደ ቤተመንግስት ተልከዋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 8/2011) የታጠቁ ወታደሮችን ወደ ቤተመንግስት የላኩት አካላት ለውጡን ለማደናቀፍ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ። በወቅቱ ለድርጊቱ የጥንቃቄ ምላሽ ባይሰጥ ኖሮ ሃገሪቱን ወደ ቀውስ የሚከታት ነበር ሲሉም ገልጸዋል። ሆኖም ሁሉም ወደ ቤተመንግስት የተንቀሳቀሱት ወታደሮች ይህንን ግንዛቤ ጨብጠው ነበር ለማለት እንደሚያስቸግርም አመልክተዋል። መስከረም 30 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት ቁጥራቸው 250 የሚሆን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከነትጥቃቸው ወደ ቤተመንግስት ያደረጉት ጉዞ ...

Read More »

አቶ ተመስገን ጥሩነህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሆኑ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 7/2011)አቶ ተመስገን ጥሩነህ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሆነው ተሾሙ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሌሎች ተጨማሪ ሶስት ግለሰቦችም ሹመት ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲወጡ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሆነው የተሾሙት አቶ አባዱላ ገመዳ በአጭር ጊዜ ውስጥ በጡረታ ከተሰናበቱ ወዲህ ስፍራው ሰው ሳይሾምበት ቆይቷል። አሁን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሆነው የተሾሙት አቶ ተመስገን ...

Read More »

በደቡብ ኢትዮጵያ በወረርሽኝ 20 ሰዎች ሞቱ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 7/2011) በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋና ወላይታ በወረርሽኝ 20 ሰዎች መሞታቸው ታወቀ። በጎፋ ዳራማሎ ወረዳ በትክትክ ወረርሽኝ 10 ሰዎች ሲሞቱ በወላይታ ኦፋ ወረዳ የቢጫ ወባ በሽታ ተከስቶ በተመሳሳይ 10 ሰዎች መሞታቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በወረርሽኝ ደረጃ የተከሰቱትን እነዚህን በሽታዎች ለመቆጣጠር በመንግስት በኩል አፋጣኝ ርምጃ ካልተወሰደ የከፋ ጉዳት ሊደርስ ይችላል ተብሏል። ትክትክ የተሰኘው በሽታ ከምድር ገጽ ላይ ጠፍቷል ከተባለ ዓመታት ተቆጥሯል። ...

Read More »