ፔትሮናስ የተባለው የነዳጅ ኩባንያ አካባቢውን ለቆ ከወጣ በሁዋላ፣ ሳውዝ ዌስት ኢነርጂ የተባለ ሃገር በቀል ኩባንያ በጋምቤላ ክልል የነዳጅ ፍለጋ ሊያካሂድ ነው

በኩባንያው ድረገጽ ላይ ላይ የሰፈረው መረጃ እንደሚያሳየው፣ ሳውዝ ዌስት ኢነርጂ  በሚቀጥሉት አራት አመታት ውስጥ በክልሉ ነዳጅ ይገኝበታል ተብሎ የሚታመንበትን 17 ሺ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ቦታን ተረክቦ ነዳጅ ያፈላልጋል።

ፔትሮናስ ኩባንያ ቀደም ብሎ በክልሉ ነዳጅ የማፈላለግ ስራ ሲሰራ ቢቆይም ፣ በጸጥታ እና በቂ መርት የለም በሚል ሰበብ አካባቢውን ለቆ መውጣቱ ያታወሳል።

ከፔትሮናስ በሁዋላ በጋምቤላ አካባቢ የነዳጅ ስራ ለማከናወን የደፈረ የውች አገር ኩባንያ አልተገኘም።

አሁን የነዳጅ አሰሳ ለማድረግ ስምምነት ከመንግስት ጋር ስምምነት የፈረመው ሳውዝ ዌስት፣ አገር በቀል ድርጅት ነው ቢባልም የኩባንያው ዋና ጽህፈት ቤት የሚገነው ግን ሆንግ ኮንግ ቻይና ውስጥ ነው።

የኩባንያው ባለቤቶች እነማን እንደሆኑ በኩባንያው ድረገጽ ላይ አልሰፈረም። የጋምቤላ እና የኦጋዴን አካባቢዎች የነዳጅ ዘይት እንዳላቸው ቢገመትም እስካሁን ድረስ ጥቅም ላይ አልዋሉም።

በአካባቢው ያለው የጸጥታ ሁኔታ መበላሸት ኩባንያዎች ስራቸውን እንዳይሰሩ በአጭር ጊዜ ውስጥም አካባቢውን እየለቀቁ እንዲሄዱ እንዳደረጋቸው ይታወቃል።