ግሎባል አልያንስ ለጌዲዮ ተፈናቃዮች በሶስት ቀን ብቻ ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሰበሰበ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 9/2011)ለጌዲዮ ተፈናቃዮች እርዳታ በግሎባል አልያንስ ዋና ዳይሬክተር ታማኝ በየነ አስተባባሪነት የተጀመረው የገንዘብ ማሳባሰብ ሂደት በሁለት ቀን ወስጥ ብቻ ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ መገኘቱ ኢትዮጵያዊያን ችግር ሲደርስባቸው በሕብረት እንደሚቆሙ ያሳየ መሆኑ ተገለጸ።

የግሎባል አልያንስ ዋና ዳይሬክተር ታማኝ በየነ በበኩሉ ኢትዮጵያዊያንን በማመስገን በጌዲዮ ያሳየነው የትብብርና የአንድነት መንፈስ በሌሎችም ጉዳዮች ላይ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

ይሕ በእንዲህ እንዳለም የአዲስ አበባ አስተዳደር ለጌዲዮ ተፈናቃዮች 30 ሚሊዮን ብር ለመርዳት ሲወስን የገቢዎች ሚንስቴር ደግሞ ከ21 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል;;