የፋኦ ሪፖርት ከ113 ሚሊየን በላይ ህዝብ በከፋ ረሃብ መጠቃቱን አስታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 25/2011)እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2018 ከ113 ሚሊየን በላይ ህዝብ በከፋ ረሃብ መጠቃቱን አንድ ሪፖርት አመለከተ።

በዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት ፋኦ አማካኝነት ይፋ በሆነው ሪፖርት ላይ እንደተመለከተው 53 ሀገራት በከፋ የረሃብ አደጋ ተመተዋል።

ከእነዚህ ሃገራት መካከል ስምንቱ አደጋው ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰባቸው በመባል መጠቀሳቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ በስምንት የዓለም ሀገራት ከ72 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የረሃብ አደጋ የገጠማቸው በሚል ተመዝግበዋል።

ከ2017 አንጻር በረሃብ የተጎዳው ህዝብ ቁጥር በ9 ሚሊየን መቀነሱን ትላንት ይፋ በሆነው ሪፖርት ተገልጿል።

በ2018 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ113ሚሊየን በላይ ህዝብ በከፋ ረሃብ መጠቃቱን አንድ ሪፖርት አመለከተ።

በዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት ፋኦ አማካኝነት ይፋ በሆነው ሪፖርት ላይ እንደተመለከተው 53 ሀገራት የረሃብ አደጋ ክፉኛ መትቷቸዋል።

ከእነዚህ ሀገራት መሀል ስምንቱ አደጋው ከፍተኛ ጉዳት ያድረሰባቸው በመባል መጠቀሳቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ ስምንት የዓለም ሀገራት ከ72 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የረሃብ አደጋ የገጠማቸው ሆነው የተመዘገቡ ናቸው ይላል ሪፖርቱ።

ከ2017 አንጻር በረሃብ የተጎዳው ህዝብ ቁጥር በ9ሚሊዮን መቀነሱን ትላንት ይፋ በሆነው ሪፖርት ተገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት የምግብ ፕሮግራምና የአውሮፓ ህብረት በተቀናጁበት የትላንቱ የፋኦ ሪፖርት 8 ሀገራትን የከፋ ረሃብ የተከሰተባቸው በሚል ጠቅሷቸዋል።

በእነዚህ 8 ሀገራት በረሃብ የተጠቃው ህዝብ ቁጥር ከአጠቃላዩ ሁለት ሶስተኛን የሚይዝ እንደሆነ ነው የተመለከተው።

ከ113 ሚሊየን በላይ ህዝብ በ53 ሀገራት በረሃብ መጠቃታቸውን ያተተው ሪፖርቱ በ8ቱ ሀገራት ከ72ሚሊየን በላይ ህዝብ ክፉኛ ጉዳት የገጠማቸው እንደሆነ አመላክቷል። ኢትዮጵያ የመን፡ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፡ አፍጋኒስታን፡ ሶርያ፡ ሱዳን፡ ደቡብ ሱዳን እና ሰሜን ናይጄሪያ በ2018 በረሃብ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ስምንቱ ሀገራት ተብለው ተጠቅሰዋል።

በዓለም አቀፉ የምግብና የእርሻ ድርጅት ፋኦ አማካኝነት ይፋ የሆነው ሪፖርት ሌላም መረጃ ይዞ ወጥቷል።

የረሃብ አደጋ ከሚያሰቃያቸው በተጨማሪ ሌሎች 42 ሀገራትም ረሃብ ሊከሰትባቸው እንደሚችል ስጋት እንዳለ አመላክቷል።

በእነዚህ 42 ሀገራት የሚገኝ ከ140 ሚሊየን በላይ ህዝብ በረሃብ ሊጠቃ እንደሚችል ምልክቶች መኖራቸውን ነው ሪፖርቱ ያመለከተው።

በ42 ሀገራት ያለው ሁኔታም ወደ ከፋ ረሃብ ለመቀየር አንድ ደረጃ ብቻ እንደሚቀረው ተገልጿል። ከ2017 አንጻር ቁጥሩ የቀነሰ ቢሆንም መጪው ጊዜ የከፋ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ፋኦ በሪፖርቱ አስጠንቅቋል።

አስቸኳይ እርዳታ ካልተገኘ በረሃብ አፋፍ ላይ የሚገኙ ሀገራት ላይም የከፋ ጉዳት እንደሚከሰት ከወዲሁ ስጋቱ ተነስቷል።

ኢትዮጵያ ከ8ሚሊየን በላይ ህዝብ በረሃብ የተጠቃባት እንደሆነች መረጃዎች ያመለክታሉ። ከ2ሚሊየን በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ የሚገኝባት ኢትዮጵያ አስቸኳይ ድጋፍ ካላገኘች ሰብዓዊ ቀውስ እንደሚከሰትባትም ተገልጿል።

የፋኦ ሪፖርት እንዳመለከተው በአየር ለውጥና በተፈጥሮአአዊ አደጋ ምክንትያት 29 ሚሊየን የዓለም ህዝብ ለረሃብ የተጋለጠ ሲሆን የምግብ ዋስትና አለመኖር ችግሩን እንዳባባሰው በሪፖርቱ ተመልክቷል።

በመረጃ ክፍተት የተነሳ በ13 ሀገራት የሚገኘውን የረሃብ ሁኔታ ለማወቅ እንዳልቻለ ያተተው የፋኦ ሪፖርት ቬንዝዌላንና ሰሜን ኮርያን በመጥቀስ ከረሃብ አንጻር ያሉበት ደረጃ ለመግለጽ አዳጋች ሲል ገልጾታል።