የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የስልጣን መልቀቂያ አስገቡ

የካቲት 10 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ከወራት በፊት በዳውሮ ዞን ዋካ ከተማ ለተነሳው ጥያቄ መንግስት ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ተቃውሞ የሚያነሱ ሰዎችን ማስፈራራት፣ የስልጣን ቦታዎችን ለመንግስት ታማኝ በሆኑ ሰዎች ማስያዝ መምረጡን የአካባቢው ሰዎች ይናገራሉ።

የመንግስት እና የህዝቡን ፍላጎት ለማጣጣም አልቻልኩም በማለት የስልጣን ጥያቄ ያቀረቡት አቶ እስራኤል ኦታሮ ፣ በአካባቢው ያለውን ችግር ለመፍታት የክልል ባለስልጣኖች ፍላጎት የሌላቸው በመሆኑ ወደ ሙያየ ተመልሼ ህዝቡን ለማገልገል እፈልጋለሁ የሚል ማመልከቻ ጽፈው ማስገባታቸውን የውስጥ ምንጮች ለኢሳት ገልጠዋል።

የክልሉ ባለስልጣናት ፣ ይህን ጥያቄህን ለህዝብ እንዳታቀርበው እኛ ችግሩን እስክንፈታ ድረስ አርፈህ ተቀመጥ ብለው እንዳስፈራሩዋቸው ምንጮች ገልጠዋል። የዞኑ አስተዳዳሪ ግን በአቋማቸው መጽናታቸው ታውቋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የወካ አስተዳዳሪ ከስልጣን እንዲወርዱ ተደርጓል። ህዝቡ ያቀረብነው ጥያቄ አልተመለሰልንም እያለ አቤቱታ ሲያቀርብ መቆየቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ዋካ ፍትህና ዲሞክራሲ በሌለበት አገር አልኖርም በማለት ራሱን በእሳት ካጋየው የኔሰው ገብሬ ሞት በሁዋላ፣ የመንግስትና የመገናኛ ብዙሀንን ትኩረት ማግኘቱዋ ተመልክቷል።

የፌደራል ፖሊስ አሁንም በአካባቢው በብዛት እንደሚገኝ ነዋሪዎች ይገልጣሉ።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide